ማርቆስ 16:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ “ድንጋዩን ከመቃብሩ ደጃፍ ማን አንከባሎ ይከፍትልናል?” በማለት እየተነጋገሩ ይሄዱ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ድንጋዩን ከመቃብሩ ደጃፍ ላይ ማን ያንከባልልልናል?” በማለት እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ድንጋዩን ከመቃብሩ ደጃፍ ላይ ማን ያንከባልልልናል?” በማለት እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስ በርሳቸውም “ድንጋዩን ከመቃብር ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል?” ይባባሉ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስ በርሳቸውም፦ ድንጋዩን ከመቃብር ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል? ይባባሉ ነበር፤ |
ይህንንም ያሉት መቃብሩ የተዘጋበት ድንጋይ እጅግ ትልቅ ስለ ነበረ ነው፤ ቀና ብለውም በተመለከቱ ጊዜ ግን ድንጋዩ ወደ ጐን ተንከባሎ አዩት።
እሑድ ጠዋት በማለዳ፥ ገና ጎሕ ሳይቀድ፥ መግደላዊት ማርያም ወደ ኢየሱስ መቃብር ሄደች፤ እዚያም እንደ ደረሰች መቃብሩ ተዘግቶበት የነበረው ድንጋይ ከመቃብሩ በር ላይ ተነሥቶ አየች።