ወዲያውኑ የኢዩ ጓደኞች የነበሩት የጦር መኰንኖች ልብሳቸውን እያወለቁ ኢዩ በሚራመድበት ደረጃ ላይ አነጠፉ፤ በዚያም ላይ እንዲቆም አድርገው እምቢልታ ነፉ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው “ኢዩ ነግሦአል!” ሲሉ ጮኹ።
ማርቆስ 11:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደቀ መዛሙርቱም የአህያውን ውርንጫ ወደ ኢየሱስ አመጡ፤ ልብሳቸውን በውርንጫው ጀርባ ላይ አድርገው ኢየሱስ ተቀመጠበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አምጥተው ልብሶቻቸውን በጀርባው ላይ አደረጉ፤ እርሱም ተቀመጠበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አምጥተው ልብሳቸውን በጀርባው ላይ አደረጉ፤ እርሱም ተቀመጠበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አመጡት፤ ልብሳቸውንም በላዩ ጣሉ፤ ተቀመጠበትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አመጡት፥ ልብሳቸውንም በላዩ ጣሉ፥ ተቀመጠበትም። |
ወዲያውኑ የኢዩ ጓደኞች የነበሩት የጦር መኰንኖች ልብሳቸውን እያወለቁ ኢዩ በሚራመድበት ደረጃ ላይ አነጠፉ፤ በዚያም ላይ እንዲቆም አድርገው እምቢልታ ነፉ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው “ኢዩ ነግሦአል!” ሲሉ ጮኹ።
ጽዮን ሆይ! ደስ ይበልሽ! ኢየሩሳሌም ሆይ! በደስታ እልል በይ! እነሆ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ፥ በአህያይቱ ማለትም በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ፥ በድል አድራጊነት ወደ አንቺ ይመጣል።