ሕዝቡን ሁሉ በአንድነት ሰብስባችሁ፥ ለተቀደሰ ጉባኤ አዘጋጁ፤ ሽማግሌዎችን ጥሩ፤ ልጆችንና ጡት የሚጠቡ ሕፃናትን ጭምር ሰብስቡ፤ ሙሽራዎችም ሳይቀሩ ከጫጒላቸው ይውጡ።
ማርቆስ 10:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ እንዲዳስሳቸው ሕፃናቱን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ሕፃናቱን ያመጡአቸውን ሰዎች ገሠጹአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ እንዲዳስሳቸው፣ ሰዎች ሕፃናትን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ገሠጿቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስ እንዲዳስሳቸው፥ ሰዎች ሕፃናትን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀመዛሙርቱ ግን ገሠጿቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲዳስሳቸውም ሕፃናትን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱም ያመጡአቸውን ገሠጹአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲዳስሳቸውም ሕፃናትን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱም ያመጡአቸውን ገሠጹአቸው። |
ሕዝቡን ሁሉ በአንድነት ሰብስባችሁ፥ ለተቀደሰ ጉባኤ አዘጋጁ፤ ሽማግሌዎችን ጥሩ፤ ልጆችንና ጡት የሚጠቡ ሕፃናትን ጭምር ሰብስቡ፤ ሙሽራዎችም ሳይቀሩ ከጫጒላቸው ይውጡ።