ማርቆስ 1:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም፦ “እኔ የመጣሁት ለማስተማር ስለ ሆነ ወንጌልን እንዳስተምር በቅርብ ወዳሉት መንደሮች እንሂድ!” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “ከዚህ ተነሥተን በአቅራቢያ ወዳሉት መንደሮች እንሂድ፤ እዚያም ልስበክ፤ የመጣሁት ለዚሁ ነውና” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፥ “ከዚህ ተነሥተን በአቅራቢያ ወዳሉት መንደሮች እንሂድ፤ እዚያም ልስበክ፤ የመጣሁት ለዚሁ ነውና” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም “በዚያ ደግሞ ልሰብክ ወደ ሌላ ስፍራ በቅርብ ወዳሉ መንደሮች እንሂድ፤ ስለዚህ መጥቻለሁና፤” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ በዚያ ደግሞ ልሰብክ ወደ ሌላ ስፍራ በቅርብ ወዳሉ መንደሮች እንሂድ ስለዚህ ወጥቻለሁና አላቸው። |
እርሱ ግን “እኔ የተላክሁት ለዚህ ስለ ሆነ ወደ ሌሎችም ከተሞች ሄጄ የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ቃል ማብሠር ይገባኛል፤” አላቸው።
የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁ፤ እነርሱም ተቀብለውታል፤ ከአንተ ዘንድ መጥቼ መምጣቴንም በእውነት ዐውቀዋል፤ አንተ እንደ ላክኸኝም አምነዋል።