ሚልክያስ 3:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ፥ ሕዝቡም ሁሉ ከእኔ ስለምትዘርፉ የተረገማችሁ ሆናችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተም፣ መላው ሕዝባችሁም ስለምትሰርቁኝ የተረገማችሁ ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ፥ ይህ ሕዝብ ሁሉ፥ ሰርቃችሁኛልና በእርግማን ርጉሞች ናችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ፥ ይህ ሕዝብ ሁሉ፥ እኔን ሰርቃችኋልና በእርግማን ርጉሞች ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ፥ ይህ ሕዝብ ሁሉ፥ እኔን ሰርቃችኋልና በእርግማን ርጉሞች ናችሁ። |
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “የተጠቀለለው መጽሐፍ በውስጡ በምድሪቱ ሁሉ ላይ የሚመጣው ርግማን ተጽፎበታል፤ የተጠቀለለው መጽሐፍ በአንድ በኩል ‘ሌባ ሁሉ ከምድር ይወገዳል’ የሚል ሲሆን፥ በሌላ በኩል ‘በመሐላ ሐሰት የሚናገር ሁሉ ይጠፋል’ ይላል።
ባታዳምጡ፥ ለስሜም ክብር ለመስጠት ቃሌን በልባችሁ ባታኖሩት መርገም እልክባችኋለሁ፤ በረከታችሁንም ወደ ርግማን እለውጣለሁ፤ እኔን ማክበር በልባችሁ ውስጥ ስለሌለ በእርግጥ ይህን ሁሉ አደርግባችኋለሁ።
የዛራ ልጅ ዓካን መደምሰስ በሚገባቸው ነገሮች እምነተቢስ ሆኖ ትእዛዝ በማፍረሱ የእግዚአብሔር ቊጣ በእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ላይ አልወረደምን? በጥፋቱም የጠፋው እርሱ ብቻ አልነበረም።’ ”