ሚልክያስ 3:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው የእግዚአብሔርን ሀብት ይዘርፋልን? ሆኖም እናንተ እኔን ዘርፋችኋል፥ እናንተ ግን እንዴት ከአንተ እንዘርፋለን ብላችሁ ትጠይቃላችሁ፤ ከእኔ የዘረፋችሁት ዐሥራትንና መባን ባለመክፈላችሁ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን ትሰርቁኛላችሁ። “እናንተ ግን፣ ‘እንዴት እንሰርቅሃለን?’ ትላላችሁ። “ዐሥራትና መባ ትሰርቁኛላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን ሰርቃችሁኛል። እናንተም፦ እንዴት እንሰርቅሃለን? ብላችኋል። በአሥራትና በቁርባን ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም፦ የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም፦ የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው። |
አንዳንድ ሰዎች በለጋሥነት ገንዘባቸውን ይበትናሉ፤ ነገር ግን ሀብታቸው እየበዛ ይሄዳል፤ ሌሎች ደግሞ ያለ ልክ ለገንዘባቸው ይሳሳሉ፤ ነገር ግን ድኽነታቸው እየበዛ ይሄዳል።
ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆኑ በጎቻችሁን አላቀረባችሁልኝም፤ በመሥዋዕታችሁም አላከበራችሁኝም፤ እኔም መባ እንድታቀርቡልኝ በመጠየቅ ሸክም አልሆንኩባችሁም፤ ‘ዕጣን አቅርቡልኝም’ ብዬ አላሰለቸኋችሁም።።
በአምስተኛው ዓመት ግን ፍሬውን ትበላላችሁ፤ ይህን ብታደርጉ ዛፎቻችሁ በየጊዜው የሚሰጡአችሁ ፍሬ ይበልጥ እየበዛ ይሄዳል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “የተጠቀለለው መጽሐፍ በውስጡ በምድሪቱ ሁሉ ላይ የሚመጣው ርግማን ተጽፎበታል፤ የተጠቀለለው መጽሐፍ በአንድ በኩል ‘ሌባ ሁሉ ከምድር ይወገዳል’ የሚል ሲሆን፥ በሌላ በኩል ‘በመሐላ ሐሰት የሚናገር ሁሉ ይጠፋል’ ይላል።
እነሆ፥ እናንተ እየተሳለቃችሁ ‘ይህ ሁሉ ምን አሰልቺ ነገር ነው!’ ትላላችሁ። የተሰረቀውን፥ አንካሳውን ወይም የታመመውን እንስሳ ለመሥዋዕትነት ታቀርባላችሁ፤ እኔ ይህን የምቀበል ይመስላችኋልን?
ለመሆኑ የታወረውን፥ የታመመውንና አንካሳ የሆነውን እንስሳ ለመሥዋዕት ስታቀርቡ በደል የፈጸማችሁ አይመስላችሁምን? ይህን የመሰለ እንስሳ ለአለቃችሁ ገጸ በረከት አድርጋችሁ ብታቀርቡለት፥ ደስ ብሎት የሚቀበላችሁና የሚያመሰግናችሁ ይመስላችኋልን?” ይላል የሠራዊት አምላክ።
እነርሱም፥ “የሮማው ንጉሠ ነገሥት ነው!” አሉት፤ እርሱም፥ “እንግዲያውስ የንጉሡን ለንጉሡ የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር ስጡ፤” አላቸው።
እንግዲህ ለበላይ ባለሥልጣን ሊደረግ የሚገባውን ሁሉ አድርጉ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን ክፈሉ፤ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።
እስራኤላውያን በድለዋል፤ እንዲጠብቁት ያዘዝኳቸውንም ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ ከተከለከሉት ነገሮች ወስደዋል፤ ሰርቀዋል፤ ከራሳቸው ንብረት ጋር በማቀላቀል አታላዮች ሆነዋል።