ሚልክያስ 1:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በነቢዩ በሚልክያስ አማካይነት ለእስራኤል ሕዝብ የተናገረው የትንቢት ቃል ይህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሚልክያስ በኩል ወደ እስራኤል የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ንግር ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሚልክያስ እጅ ለእስራኤል የሆነ የጌታ ቃል ይህ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሚልክያስ እጅ ለእስራኤል የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ሸክም ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሚልክያስ እጅ ለእስራኤል የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ሸክም ይህ ነው። |
እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፥ “ኤርምያስ ሆይ! ነቢይ ወይም ካህን ወይም ከሕዝቤ አንዱ፥ ‘የእግዚአብሔር ሸክም ምንድን ነው?’ ብሎ ቢጠይቅህ፥ ‘የእግዚአብሔር ሸክም እናንተ ናችሁ፤ ስለ ሆነም ከፊቱ ያስወግዳችኋል’ ብለህ ንገራቸው።
ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፥ ስድስተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን፥ እግዚአብሔር በነቢዩ አማካይነት በሐጌ ተናገረ የተናገረውም የይሁዳ ገዢ ለነበረው ለሰላትያል ልጅ ለዘሩባቤልና ሊቀ ካህናት ለነበረው ለኢዮሴዴቅ ልጅ ለኢያሱ ነው።
የይሁዳ ሕዝብ እምነተቢስ ሆኖአል፤ በእስራኤልና በኢየሩሳሌም አጸያፊ የርኲሰት ሥራ ፈጽመዋል፤ ይህም የሆነው ጣዖት አምላኪዎች የሆኑ የባዕድ ሴቶችን በማግባት ይሁዳ እግዚአብሔር የሚወደውን ቤተ መቅደስ ስላረከሰ ነው።