ሉቃስ 8:49 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ገና ይህንን በመናገር ላይ ሳለ አንድ ሰው ከምኲራብ አለቃው ከኢያኢሮስ ቤት መጥቶ “ልጅህ ሞታለች፤ እንግዲህ መምህሩን በከንቱ አታድክመው!” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ገና እየተናገረ ሳለ፣ አንድ ሰው ከምኵራብ አለቃው ከኢያኢሮስ ቤት መጥቶ፣ “ልጅህ ሞታለች፤ ከዚህ በኋላ መምህሩን አታድክመው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ይህን እየተናገረ ሳለ አንድ ሰው ከምኵራብ አለቃው ቤት መጥቶ፦ “ልጅህ ሞታለች፤ እንግዲህ መምህሩን አታድክም፤” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም ሲናገር አንድ ሰው ከምኵራቡ ሹም ቤት መጥቶ፥ “ልጅህስ ሞታለች እንግዲህ መምህሩን አታድክመው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ገና ሲናገር አንድ ሰው ከምኵራብ አለቃው ቤት መጥቶ፦ ልጅህ ሞታለች፤ እንግዲህ መምህሩን አታድክም አለ። |
ኢየሱስ ይህን ሲነግራቸው ሳለ፥ አንድ የምኲራብ አለቃ ወደ እርሱ መጣ፤ በግንባሩም በኢየሱስ ፊት ተደፍቶ፥ “እነሆ፥ ልጄ አሁን ሞተችብኝ፤ ነገር ግን አንተ መጥተህ እጅህን ብትጭንባት ትድናለች” አለው።
ታዲያ፥ ያ ወዳጁ ከውስጥ ሆኖ፥ ‘እባክህ አታስቸግረኝ! በሩ ተቈልፎአል፤ ልጆቼም ከእኔ ጋር በአልጋ ላይ ተኝተዋል፤ ስለዚህ ተነሥቼ የፈለግኸውን እንጀራ ልሰጥህ አልችልም፤’ ይለዋልን?
ስለዚህ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር አብሮ ሄደ፤ ወደ ቤቱም በቀረበ ጊዜ የመቶ አለቃው ወዳጆቹን እንዲህ ሲል ወደ ኢየሱስ ላከ፦ “ጌታ ሆይ፥ አንተ ወደ ቤቴ ትገባ ዘንድ ያልተገባሁ ነኝና ወደ ቤቴ ለመምጣት አትድከም።