ሉቃስ 8:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ቀን ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በጀልባ ተሳፈረና “ወደ ባሕሩ ማዶ እንሻገር፤” አላቸው፤ እነርሱም ለመሄድ ተነሡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዕለታቱ በአንድ ቀን፣ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ጀልባ ላይ ወጣ፤ ኢየሱስም፤ “ወደ ባሕሩ ማዶ እንሻገር” አላቸው፤ ከዚያም ጕዞ ቀጠሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዕለታቱም በአንዱ ቀንም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ታንኳ ገብቶ፦ “ወደ ባሕር ማዶ እንሻገር፤” አላቸው፤ እነርሱም ለመሄድ ተነሡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዕለታት በአንዲት ቀንም እንዲህ ሆነ፤ እርሱ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ታንኳ ወጣና፥ “ኑ ወደ ባሕሩ ማዶ እንሻገር” አላቸው እነርሱም ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዕለታቱም በአንዱ እርሱ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ታንኳ ገብቶ፦ ወደ ባሕር ማዶ እንሻገር አላቸው፤ ተነሡም። |
በባሕሩ ላይ እየቀዘፉ ሲሄዱ ሳሉ ኢየሱስ አንቀላፋ፤ በዚያን ጊዜ ብርቱ ዐውሎ ነፋስ በባሕሩ ላይ ተነሣ፤ ውሃውም በጀልባው ውስጥ መሙላት ስለ ጀመረ አደጋው አስግቶአቸው ነበር።
በእስያ የባሕር ዳርቻ ወዳሉት ወደቦች በሚሄደው የአድራሚጥዮን መርከብ ተሳፍረን ተጓዝን፤ በተሰሎንቄ የሚኖረው የመቄዶንያው ሰው አርስጥሮኮስም ከእኛ ጋር ነበረ።