ከዚያም በኋላ ኢየሱስ በማቴዎስ ቤት በማእድ ተቀምጦ ሳለ ብዙ ቀራጮችና ኃጢአተኞች፥ ወደዚያ መጥተው ከእርሱና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በማእድ ተቀመጡ።
ሉቃስ 7:49 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእርሱ ጋር በማእድ ይበሉ የነበሩትም “ኃጢአትን እንኳ ይቅር የሚል ይህ ማነው?” እያሉ በልባቸው ያስቡ ጀመር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐብረውት በማእድ ተቀምጠው የነበሩ እንግዶችም፣ “ይህ ኀጢአትን እንኳ የሚያስተሰርይ እርሱ ማን ነው?” ብለው በልባቸው አሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጠው የነበሩት በልባቸው፦ “ኃጢአትን እንኳ የሚያስተሰርይ ይህ ማን ነው?” ይሉ ጀመር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በማዕዱ የተቀመጡትም እርስ በርሳቸው፥ “ኀጢአትን የሚያስተሰርይ ይህ ማነው?” ይሉ ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጠው የነበሩት በልባቸው፦ ኃጢአትን እንኳ የሚያስተሰርይ ይህ ማን ነው? ይሉ ጀመር። |
ከዚያም በኋላ ኢየሱስ በማቴዎስ ቤት በማእድ ተቀምጦ ሳለ ብዙ ቀራጮችና ኃጢአተኞች፥ ወደዚያ መጥተው ከእርሱና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በማእድ ተቀመጡ።