ሉቃስ 7:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ‘እነሆ! እፊት እፊትህ እየሄደ መንገድህን የሚያዘጋጅ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥’ ተብሎ የተጻፈለት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህ ተብሎ የተጻፈለት እርሱ ነው፤ “ ‘መንገድህን በፊትህ የሚያዘጋጅ መልእክተኛዬን ከአንተ አስቀድሜ እልካለሁ።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነሆ፥ መንገድህን አስቀድሞ የሚያዘጋጅ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ” ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልእክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ፥ ተብሎ ስለ እርሱ የተጻፈለት ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነው። |
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ በፊቴ መንገድን ያዘጋጅ ዘንድ መልእክተኛዬን እልካለሁ፤ የምትፈልጉት ጌታም በድንገት ወደ ቤተ መቅደሱ ይመጣል፤ በእርሱ የምትደሰቱበት የቃል ኪዳን መልእክተኛም በእርግጥ ይመጣል።”