ሉቃስ 6:49 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቃሌን ሰምቶ የማይፈጽም ግን ያለ መሠረት ቤቱን በዐፈር ላይ የሠራ ሰውን ይመስላል፤ ጐርፍ መጥቶ ያንን ቤት በገፋው ጊዜ ወዲያውኑ ወደቀ፤ አወዳደቁም እጅግ ታላቅ ሆነ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቃሌን ሰምቶ የማይፈጽም ግን ቤቱን ያለ መሠረት በዐፈር ላይ የሠራን ሰው ይመስላል፤ የወንዝ ሙላትም ቤቱን በመታው ጊዜ ወዲያው ወደቀ፤ ክፉኛም ፈራረሰ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ሰምቶ የማያደርገው ቤቱን ያለ መሠረት በምድር ላይ የሠራ ሰውን ይመስላል፤ ወንዙም ገፋው፤ ወዲያውም ወደቀ የዚያ ቤት አወዳደቅም ታላቅ ሆነ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ግን ቤቱን ያለ መሠረት በአፈር ላይ የሠራ ሰውን ይመስላል፤ ጎርፎች ገፉት፤ ወዲያውኑም ወደቀ፤ የዚያም ቤት አወዳደቁ ታላቅ ሆነ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰምቶ የማያደርገው ግን ያለ መሠረት በምድር ላይ ቤቱን የሠራ ሰውን ይመስላል፤ ወንዙም ገፋው ወዲያውም ወደቀ የዚያ ቤት አወዳደቅም ታላቅ ሆነ። |
ስለዚህም ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት ሕዝቤ አንተ ምን እንደምትናገር ለማዳመጥ ብቻ ይሰበሰባሉ፤ ነገር ግን የምትነግራቸውን ሁሉ አይፈጽሙም፤ የምትናገረውን ቃል የሚወዱት መስለው ይታያሉ፤ ነገር ግን ከበዝባዥነታቸው አይመለሱም፤
ይሁን እንጂ ሴቶች ልጆቻችሁ ዘማውያት ምራቶቻችሁም አመንዝሮች ስለ ሆኑ አልቀጣቸውም፤ ምክንያቱም እናንተ ወንዶች ራሳችሁ በቤተ መቅደስ የሚሴስኑ ሴቶችን ተከትላችሁ ከእነርሱ ጋር ባዕድ አምልኮ ትፈጽማላችሁ፤ ስለዚህ ማስተዋል የጐደለው ሕዝብ ይጠፋል።
ግን እነርሱ ለጊዜው ነው እንጂ በልባቸው ውስጥ ሥር አልሰደደም፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ በቃሉ ምክንያት ችግር ወይም ስደት ቢደርስባቸው ወዲያውኑ ተሰናክለው ይወድቃሉ።
እርሱ በጥልቅ ቆፍሮ ቤቱን በጽኑ አለት ላይ የመሠረተውን ሰው ይመስላል፤ ጐርፍ መጥቶ ያንን ቤት ገፋው፤ ነገር ግን በጽኑ መሠረት ላይ ስለ ተሠራ ሊያነቃንቀው አልቻለም።
በእኔ ላይ ያለውን ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ አባቴ ቈርጦ ይጥለዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ግን አብዝቶ እንዲያፈራ ገርዞ ያጠራዋል።
ብዙ ጊዜ በየምኲራቡ እንዲቀጡና በጌታ ላይ የስድብ ቃል እንዲናገሩ አስገድዳቸው ነበር፤ በእነርሱ ላይ በጣም ተቈጥቼም ወደ ሌሎች የውጪ አገር ከተሞች እንኳ ወጥቼ እየሄድኩ አሳድዳቸው ነበር።
በዚህ ምክንያት ከእንግዲህ ወዲህ በትዕግሥት መጠበቅ ባለመቻሌ ስለ እምነታችሁ ማወቅ ፈልጌ ጢሞቴዎስን ወደ እናንተ ላክሁት፤ እርሱን የላክሁትም ምናልባት ፈታኙ በአንድ መንገድ ፈትኖአችሁ ይሆናል፤ ሥራችንም ከንቱ ሆኖ ቀርቶአል በማለት ፈርቼ ነው።
ጌታችንንና አዳኛችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቅ ከዓለም ርኲሰት ካመለጡ በኋላ ተመልሰው በዚያው ርኲሰት ተይዘው ቢሸነፉ ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው ሁኔታቸው የባሰ ይሆንባቸዋል፤
እነርሱ የወጡት ከእኛ መካከል ነው። ይሁን እንጂ ዱሮውንም ከእኛ ወገን አልነበሩም። ከእኛ ወገን ቢሆኑማ ኖሮ ከእኛ ጋርም ጸንተው በኖሩ ነበር። ነገር ግን ሁሉም ከእኛ ወገን አለመሆናቸው እንዲታወቅ ከእኛ መካከል ተለይተው ወጥተዋል።