ንጉሡ ኢዮርብዓም “እባክህ እጄን ያድንልኝ ዘንድ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልኝ!” ሲል የእግዚአብሔርን ነቢይ ለመነው። የእግዚአብሔርም ነቢይ ወደ እግዚአብሔር ጸልዮለት የንጉሡ እጅ ዳነች። እንደ ቀድሞም ሆነች።
ሉቃስ 6:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚረግሙአችሁን መርቁ፤ ለሚበድሉአችሁም ጸልዩላቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚረግሟችሁን መርቁ፤ ለሚበድሏችሁም ጸልዩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ስለሚበድሉአችሁም ጸልዩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚረግሙአችሁን መርቁአቸው፤ ለሚበድሉአችሁም ጸልዩላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ስለሚበድሉአችሁም ጸልዩ። |
ንጉሡ ኢዮርብዓም “እባክህ እጄን ያድንልኝ ዘንድ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልኝ!” ሲል የእግዚአብሔርን ነቢይ ለመነው። የእግዚአብሔርም ነቢይ ወደ እግዚአብሔር ጸልዮለት የንጉሡ እጅ ዳነች። እንደ ቀድሞም ሆነች።
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ፍልስጥኤማውያን በማያቋርጥ ጠላትነት በቀልን ተበቅለዋል፤ ይህም የጥፋት በቀል ተንኰልን በተመላ ልብ ነበር።
“በኀይለኛ ቅናቴ በሌሎች ሕዝቦች ላይና በመላዋ ኤዶም ላይ እናገራለሁ፤ እነርሱ ደስታን በተመላ ስሜትና በፍጹም ንቀት መሰማሪያዋን ለመውረር ምድሬን ርስታቸው አደረጉት፤ ይላል ልዑል እግዚአብሔር።
እኔ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁን መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁ በጎ አድርጉ፤ ክፉ ለሚያደርጉባችሁና ለሚያሳድዱአችሁ ጸልዩ” እላችኋለሁ።
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ፦ “አባት ሆይ! የሚያደርጉትን ስለማያውቁ ይቅር በላቸው!” አለ። ወታደሮቹም ዕጣ ተጣጥለው የኢየሱስን ልብስ ተከፋፈሉ።
እናንተ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ! መልካም ነገርም አድርጉላቸው፤ ‘ብድራችን ይመለስልናል’ ብላችሁ ተስፋ ሳታደርጉ አበድሩ፤ ይህን ብታደርጉ ዋጋችሁ ትልቅ ይሆናል፤ የልዑል እግዚአብሔር ልጆችም ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለውለታ ቢሶችና ለክፉዎች እንኳ ሳይቀር ቸር ነው።