ሉቃስ 6:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የያዕቆብ ልጅ ይሁዳና ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠው አስቆሮታዊው ይሁዳ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የያዕቆብ ልጅ ይሁዳና ኋላ አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የያዕቆብ ልጅ ይሁዳና ከሐዲ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳም ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የያዕቆብ ወንድም ይሁዳ፥ የከዳውና አሳልፎ የሰጠው ያስቆሮቱ ሰው ይሁዳም ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የያዕቆብ ይሁዳም፥ አሳልፎ የሰጠውም የአስቆሮቱ ይሁዳ ናቸው። |
ኢየሱስ ከሐዋርያቱ ጋር ከተራራው ወርዶ በሜዳ ላይ ቆመ፤ ከደቀ መዛሙርቱም ብዙዎቹ በዚያ ነበሩ፤ እንዲሁም ሊሰሙትና ከበሽታቸው ሊፈወሱ ፈልገው የመጡ፥ እጅግ ብዙ ሕዝብ ነበሩ። እነርሱም የመጡት ከይሁዳ ምድር ከኢየሩሳሌም ከተማ፥ በባሕር አጠገብ ከሚገኙት ከጢሮስና ከሲዶና ከተሞች ነበር።
የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና የያዕቆብ ወንድም ከሆነው ከይሁዳ፥ ለተጠራችሁት፥ በእግዚአብሔር አብ ለተወደዳችሁት፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለተጠበቃችሁት ሁሉ፥