ነገር ግን ለእነርሱ እንቅፋት እንዳንሆንባቸው ወደ ባሕር ሂድና መንጠቆ ጣል፤ በመጀመሪያ የሚወጣውን ዓሣ ያዝ፤ አፉንም ስትከፍት በውስጡ ገንዘብ ታገኛለህ፤ ያንንም ወስደህ ስለ እኔና ስለ አንተ ክፈል።”
ሉቃስ 5:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንግግሩንም ከጨረሰ በኋላ ስምዖንን፦ “ጀልባዋን ወደ ጥልቁ ባሕር ራቅ አድርገህ አንተና ጓደኞችህ ዓሣ ለማጥመድ መረባችሁን ጣሉ፤” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ስምዖንን፣ “ወደ ጥልቁ ውሃ ፈቀቅ በልና ዓሣ ለመያዝ መረባችሁን ጣሉ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንግግሩንም ከጨረሰ በኋላ፥ ስምዖንን፦ “ወደ ጥልቁ ፈቀቅ በል፤ መረቦቻችሁንም ለማጥመድ ጣሉ፤” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትምህርቱንም ከፈጸመ በኋላ ስምዖንን፥ “ወደ ጥልቁ ባሕር ፈቀቅ በል፤ መረቦቻችሁንም ለማጥመድ ጣሉ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገሩንም ከጨረሰ በኋላ፥ ስምዖንን፦ ወደ ጥልቁ ፈቀቅ በል መረቦቻችሁንም ለማጥመድ ጣሉ አለው። |
ነገር ግን ለእነርሱ እንቅፋት እንዳንሆንባቸው ወደ ባሕር ሂድና መንጠቆ ጣል፤ በመጀመሪያ የሚወጣውን ዓሣ ያዝ፤ አፉንም ስትከፍት በውስጡ ገንዘብ ታገኛለህ፤ ያንንም ወስደህ ስለ እኔና ስለ አንተ ክፈል።”
እርሱም “መረቡን ከጀልባው በስተቀኝ በኩል ጣሉና ታገኛላችሁ” አላቸው። ስለዚህ መረቡን በባሕሩ ውስጥ ጣሉት፤ ብዙ ዓሣም ከመያዛቸው የተነሣ መረቡን መጐተት አቃታቸው።