ሉቃስ 4:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ አንተ ለእኔ ብትሰግድልኝ ይህ ሁሉ የአንተ ይሆናል፤” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ብትሰግድልኝ ይህ ሁሉ የአንተ ይሆናል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ አንተ በእኔ ፊት ብትሰግድ፥ ሁሉ ለአንተ ይሆናል፤” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ አንተ በፊቴ ብትሰግድልኝ ይህ ሁሉ ለአንተ ይሁንልህ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ አንተ በእኔ ፊት ብትሰግድ፥ ሁሉ ለአንተ ይሆናል አለው። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የግብጽ ሀብትና የኢትዮጵያ ሸቀጥ ለእናንተ ተላልፎ ይሰጣል፤ ቁመታቸው ረጃጅም የሆነ የሳባ ሰዎችም በሰንሰለት ታስረው በመምጣት ይከተሉአችኋል፤ እጅ ነሥተውም፦ ‘እግዚአብሔር የሚገኘው በእናንተ ዘንድ ብቻ ነው፤ በሌላ አይደለም፤ ከእርሱም በቀር ሌላ አምላክ የለም’ ይላሉ።”
አንዳንድ ሰዎች ኰረጆአቸውን ከፍተው ወርቅ እንደ ልባቸው ይመዛሉ፤ ብሩንም በሚዛን ይመዝናሉ፤ ጣዖት አድርጎ እንዲሠራላቸውም አንጥረኛ ይቀጥራሉ፤ ከተሠራም በኋላ እየሰገዱ ያመልኩታል።
ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር ሆኖ አዩት፤ ተደፍተውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው የወርቅ፥ የዕጣንና የከርቤ ስጦታ አቀረቡለት።
ኢየሱስን ባየ ጊዜ ጮኸ፤ በኢየሱስ ፊትም ወደቀና ድምፁን ከፍ አድርጎ፥ “አንተ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ከእኔ ጋር ምን ጉዳይ አለህ? እባክህ አታሠቃየኝ፤” አለው።
እነዚህን ነገሮች የሰማሁና ያየሁ እኔ ዮሐንስ ነኝ፤ እነዚህን ነገሮች በሰማሁና ባየሁ ጊዜ እነዚህን ነገሮች ላሳየኝ መልአክ ልሰግድለት በእግሩ ሥር ወደቅኩ።
ኻያ አራቱ ሽማግሌዎች ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሚኖረው፥ በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ፊት በግንባራቸው ተደፍተው ይሰግዳሉ፤ አክሊሎቻቸውንም በዙፋኑ ፊት አኑረው፥ እንዲህ ይላሉ፦
የብራናውን ጥቅል መጽሐፍ በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ኻያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት በግንባራቸው ተደፉ፤ እያንዳንዳቸው በገና ይዘው ነበር፤ እንዲሁም የቅዱሳን ጸሎት የሆነው ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ሙዳይ ይዘው ነበር።