ሉቃስ 3:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ በአውድማ ላይ እህሉን ከገለባ ለመለየት መንሹን በእጁ ይዞአል፤ ካጣራውም በኋላ ጥሩውን እህል በጐተራው ይከታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐውድማውን ፈጽሞ ለማጥራትና ስንዴውንም ወደ ጐተራው ለመክተት መንሹ በእጁ ነው፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አውድማውን ፈጽሞ ለማጥራትና ስንዴውን በጎተራው ለመክተት መንሹ በእጁ ነው፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንሹ በእጁ ነው፤ የዐውድማውንም እህል ያጠራል፤ ስንዴውንም በጎተራው ይሰበስባል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥላል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንሹም በእጁ ነው፥ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፥ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል አላቸው። |
ገለባ በነፋስ እንደሚበተን፥ በምድሪቱ ውስጥ ባሉት ከተሞች ሁሉ በተንኳችሁ፤ ከክፉ ሥራችሁም ካለመመለሳችሁ የተነሣ፥ እናንተን ሕዝቤን አጠፋኋችሁ፤ ልጆቻችሁ ሁሉ እንዲገደሉ አደረግሁ።
እነዚህ ሕዝቦች ግን የእግዚአብሔርን ዕቅድ አላወቁም፤ የሚወቃ የእህል ነዶ በአውድማ ላይ እንደሚሰበሰብ እግዚአብሔር እነርሱን ራሳቸውን የሰበሰባቸው ለቅጣት መሆኑን አልተገነዘቡም።
ስለዚህ ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ ድረስ ስንዴውም እንክርዳዱም አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜ ዐጫጆችን እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ንቀሉ፤ በእሳት እንዲቃጠልም በየነዶው እሰሩ፤ ስንዴውን ግን ሰብስቡና በጐተራዬ ክተቱ’ እላቸዋለሁ።”
እርሱ መንሹ በእጁ ነው። በእርሱም አውድማውን ደኅና አድርጎ ያጠራል። ስንዴውን በጐተራ ይከተዋል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”