Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 30:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 የምታርሱባቸው በሬዎችና አህዮች በጨው የታሸ መኖና በመንሽና በአካፋ ተገለባብጦ የጠራውን ገፈራ ይመገባሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 የዕርሻ በሬዎችና አህዮች በመንሽና በላይዳ የተለየውን ገፈራና ድርቆሽ ይበላሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 መሬትንም የሚያርሱ በሬዎችና አህዮች በመንሽና በወንፊት የነጻውን ጨው ጨው የሚለውን ገፈራ ይበላሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 መሬ​ት​ንም የሚ​ያ​ርሱ በሬ​ዎ​ችና አህ​ዮች በመ​ን​ሽና በወ​ን​ፊት የነ​ጻ​ውን ከገ​ብስ ጋር የተ​ቀ​ላ​ቀ​ለ​ውን ገፈራ ይበ​ላሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 መሬትንም የሚያርሱ በሬዎችና አህዮች በመንሽና በወንፊት የነጻውን ጨው ጨው የሚለውን ገፈራ ይበላሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 30:24
10 Referencias Cruzadas  

በቤታችን ብዙ ገለባና ድርቆሽ አለ፤ ለእናንተም ማደሪያ ቦታ ይገኛል” አለችው።


በምድር ላይ ራብ ከገባ ሁለተኛ ዓመቱን ይዞአል፤ ሰዎች አርሰው መከር መሰብሰብ የማይችሉባቸው አምስት ዓመቶች ገና ይመጣሉ።


“ሥራችሁን ሁሉ የምታከናውኑባቸው ስድስት ቀኖች አሉላችሁ፤ በእርሻም ሆነ በመከር ወራት በሰባተኛው ቀን ምንም ሥራ አትሥሩ።


በየውሃው ምንጭ አጠገብ ዘራችሁን ስለምትዘሩና ለከብቶቻችሁና ለአህዮቻችሁ በቂ መሰማርያ ስለምታገኙ በበረከት የተሞላችሁ ትሆናላችሁ።


እርሱ መንሹ በእጁ ነው። በእርሱም አውድማውን ደኅና አድርጎ ያጠራል። ስንዴውን በጐተራ ይከተዋል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”


እርሱ በአውድማ ላይ እህሉን ከገለባ ለመለየት መንሹን በእጁ ይዞአል፤ ካጣራውም በኋላ ጥሩውን እህል በጐተራው ይከታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”


እርስዋንም ጨርሶ ወዳልታረሰና ምንም ተክል ወዳልተተከለበት፥ ወንዙም ወደማይደርቅበት ሸለቆ ይዘዋት ወርደው በዚያ አንገትዋን በመቈልመም ይስበሩት፤


“እህል በምታበራይበት ጊዜ የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር።


ከእነርሱም አንዳንዶቹን የሺህ አለቆችና የኀምሳ አለቆች አድርጎ ይሾማል፤ ወንዶቹ ልጆቻችሁ የንጉሡ ሁዳድ አራሾችና መከር ሰብሳቢዎች ይሆናሉ፤ ሌሎችም የጦር መሣሪያና የሠረገላ ዕቃ ሠራተኞች ይሆናሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos