ከዚያም ከዐሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ ርኩስ መንፈስ ጀርባዋን ያጐበጣት አንዲት ሴት ነበረች፤ እርስዋ ወገብዋ በመጒበጡ ቀና ለማለት በፍጹም አትችልም ነበር።
ሉቃስ 21:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ሁሉ መሆን በሚጀምርበት ጊዜ መዳናችሁ ቀርቦአልና ቀና ብላችሁ ወደ ላይ ተመልከቱ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተም እነዚህ ነገሮች መፈጸም ሲጀምሩ፣ መዳናችሁ ስለ ተቃረበ ቀጥ ብላችሁ ቁሙ፤ ራሳችሁንም ወደ ላይ ቀና አድርጉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም መሆን ሲጀምር መዳናችሁ ቀርቦአልና ቁሙ፤ ቀናም በሉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህም ሁሉ በሆነ ጊዜ ወደ ላይ አቅንታችሁ ተመልከቱ፤ ራሳችሁንም አንሡ፤ የሚያድናችሁ መጥቶአልና።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም ሊሆን ሲጀምር ቤዛችሁ ቀቦአልና አሻቅባችሁ ራሳችሁን አንሡ። |
ከዚያም ከዐሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ ርኩስ መንፈስ ጀርባዋን ያጐበጣት አንዲት ሴት ነበረች፤ እርስዋ ወገብዋ በመጒበጡ ቀና ለማለት በፍጹም አትችልም ነበር።
ነገር ግን በመቃተት ላይ ያለው ፍጥረት ብቻ አይደለም፤ የመጀመሪያውን የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ የተቀበልን እኛም የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን የእግዚአብሔር ልጆች መሆንን በተስፋ እየተጠባበቅን በውስጣዊ ሰውነታችን በመቃተት ላይ እንገኛለን፤