እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በግብጽ ምድር የእርስ በርስ ጦርነት እንዲቀሰቀስ አደርጋለሁ፤ ወንድም በወንድሙ ላይ፥ ጐረቤትም በጐረቤቱ ላይ በጠላትነት እንዲነሣ አደርጋለሁ፤ ከተሞች በከተሞች ላይ፥ ነገሥታት በነገሥታት ላይ በጠላትነት ተነሥተው ይዋጋሉ።
ሉቃስ 21:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀጥሎም እንዲህ አላቸው፤ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ እንዲህ አላቸው “ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም አላቸው፥ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ ነገሥታትም በነገሥታት ላይ ይነሣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣል፤ |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በግብጽ ምድር የእርስ በርስ ጦርነት እንዲቀሰቀስ አደርጋለሁ፤ ወንድም በወንድሙ ላይ፥ ጐረቤትም በጐረቤቱ ላይ በጠላትነት እንዲነሣ አደርጋለሁ፤ ከተሞች በከተሞች ላይ፥ ነገሥታት በነገሥታት ላይ በጠላትነት ተነሥተው ይዋጋሉ።
ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ጦርነት ያነሣል፤ በየስፍራው የምድር መናወጥና ራብ ይሆናል፤ ይህ ሁሉ እንደ ምጥ ጣር ያለ የጭንቅ መጀመሪያ ነው።
ከእነርሱም አንዱ አጋቦስ የሚባለው ተነሥቶ በዓለም ሁሉ ታላቅ ራብ እንደሚሆን በመንፈስ ቅዱስ አነሣሽነት ትንቢት ተናገረ፤ ይህም የሆነው በሮም ንጉሠ ነገሥት በቀላውዴዎስ ዘመን ነበር።
ይህ “አንድ ጊዜ ደግሜ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የማይናወጡ ነገሮች ጸንተው እንዲኖሩ የሚናወጡ ወይም የተፈጠሩ ነገሮች መወገዳቸውን ነው።