ሉቃስ 20:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ከሰው ነው’ ብንል ደግሞ ሕዝቡ ሁሉም በዮሐንስ ነቢይነት ስለሚያምኑ በድንጋይ ይወግሩናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ከሰው’ ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስ ነቢይ መሆኑን ስለሚያምኑ በድንጋይ ይወግሩናል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ከሰዎች’ ብንል ግን ሕዝቡ ሁሉ በድንጋይ ይወግሩናል፤ ምክንያቱም ዮሐንስ ነቢይ እንደ ነበረ ሁሉም ያምኑ ነበርና” አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሰው ነው ብንለውም ሕዝቡ ሁሉ በድንጋይ ይወግሩናል፤ ሁሉም ዮሐንስ ነቢይ እንደ ሆነ አምነውበታልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰው ብንል ግን ሕዝቡ ሁሉ ይወግሩናል፤ ዮሐንስ ነቢይ እንደ ነበረ ሁሉ ያምኑ ነበርና አሉ። |
የአይሁድ አለቆች ኢየሱስ የተናገረው ምሳሌ እነርሱን የሚመለከት መሆኑን ስለ ተገነዘቡ ሊይዙት ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈርተው ትተውት ሄዱ።
ወዲያውኑ የቤተ መቅደሱ የዘበኞች አለቃና ሎሌዎቹ ሄደው አመጡአቸው፤ ያመጡአቸውም በኀይል ሳይሆን በማግባባት ነው፤ ይህንንም ያደረጉት ሕዝቡ በድንጋይ እንዳይወግራቸው በመፍራት ነው።