ሉቃስ 20:42 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት እኮ ራሱ በመዝሙር መጽሐፍ ውስጥ፦ ‘ጌታ ለጌታዬ ጠላቶችህን በእግርህ ሥር እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው’ ይላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም ራሱ ዳዊት በመዝሙር መጽሐፉ እንዲህ ብሏል፤ “ ‘ጌታ ጌታዬን፣ “በቀኜ ተቀመጥ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም ራሱ በመዝሙራት መጽሐፍ፦ “ጌታ ጌታዬን እንዲህ አለው፦ በቀኜ ተቀመጥ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ራሱ ዳዊት በመዝሙር መጽሐፍ ‘ጌታ ጌታዬን በቀኜ ተቀመጥ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ራሱ በመዝሙራት መጽሐፍ፦ ጌታ ጌታዬን፦ ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ይላል። |
ኢየሱስም፥ “ከእናንተ ጋር በነበርኩ ጊዜ ለሙሴ በተሰጠው ሕግ፥ በነቢያትና በመዝሙር መጻሕፍት ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ መፈጸም አለበት ብዬ የነገርኳችሁ ቃል ይህ ነው” አላቸው።
“ይህም የሆነበት ምክንያት በመዝሙር መጽሐፍ፥ ‘መኖሪያው ባዶ ይሁን፤ ማንም አይኑርበት፤ ደግሞም ሹመቱን ሌላ ሰው ይውሰድበት’ የሚል ተጽፎ ስለ ነበር ነው።