ሉቃስ 20:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ግን ተንኰላቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ግን ተንኰላቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ግን ተንኰላቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተንኰላቸውንም ዐውቆ፥ “ለምን ትፈትኑኛላችሁ? ገንዘቡን አሳዩኝ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ግን ተንኰላቸውንም ተመልክቶ፦ ስለ ምን ትፈትኑኛላችሁ? አንድ ዲናር አሳዩኝ፤ |
ስለዚህ ኢየሱስን ለመያዝ ምቹ ጊዜ ይጠብቁ ነበር። ለገዥው ሥልጣንና ፍርድ አሳልፈው ለመስጠት የሚያስችላቸውን የወንጀል ቃል ከእርሱ ለማግኘት ይፈልጉ ነበር፤ ስለዚህ ቅን ሰዎች መስለው፥ በንግግሩ የሚያጠምዱትን ሰላዮች ላኩበት።
“እስቲ ገንዘቡን አሳዩኝ፤ በዚህ ገንዘብ ላይ የተቀረጸው መልክና የተጻፈው ስም የማን ነው?” እነርሱም “የሮም ንጉሠ ነገሥት ነው” አሉት።
ከእንግዲህ ወዲህ በሰዎች የተንኰል ሽንገላና አታላይነት በተዘጋጀ በአሳሳች የትምህርት ነፋስና ሞገድ ወዲያና ወዲህ ተገፍትረው እንደሚወሰዱ ሕፃናት አንሆንም።
ከእግዚአብሔር ፊት የሚሰወር ምንም ፍጥረት የለም፤ በእርሱ ዐይን ፊት ሁሉ ነገር ግልጥና ዕርቃኑን ሆኖ የሚታይ ነው፤ እኛም መልስ መስጠት የሚገባን በእርሱ ፊት ነው።