ሉቃስ 2:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቤተልሔም ከተማ ሳሉ ማርያም የመውለጃዋ ጊዜ ደረሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም እንዳሉ የምትወልድበት ጊዜ ደረሰ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ሳሉ የመውለጃዋ ወራት ደረሰ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ሳሉም የምትወልድበት ቀን ደረሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ሳሉ የመውለጃዋ ወራት ደረሰ፥ |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አንቺ በኤፍራታ ምድር የምትገኚ ቤተልሔም ሆይ! ከይሁዳ ትናንሽ ከተሞች አንድ ብትሆኚም እንኳ ከአንቺ አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘለዓለም የሆነ የእስራኤልን ሕዝብ የሚመራ ገዢ ይወጣልኛል።”
በዚያም የበኲር ልጅዋን ወለደች፤ በመታቀፊያ ጨርቅ ጠቀለለችው፤ በእንግዶች ማደሪያ ስፍራ ስላላገኙ በበረት በከብቶች መመገቢያ ግርግም ውስጥ አስተኛችው።