ሉቃስ 2:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም በጌታ ሕግ “ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች ለመሥዋዕት ማቅረብ ይገባል” የሚል ትእዛዝ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም በጌታ ሕግ፣ “ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች እንደ ተባለ፣” መሥዋዕት ለማቅረብ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም በጌታ ሕግ እንደተባለው፦ “ሁለት ዋኖሶችን ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶችን” መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔርም ሕግ እንደ ታዘዘ ሁለት ዋኖስ ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ስለ እርሱ መሥዋዕት አድርገው ያቀርቡለት ዘንድ። |
“አንድ ሰው ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ማቅረብ ባይችል፥ አንድ ኪሎ የላመ ዱቄት ስለ ኃጢአቱ ስርየት የሚቀርብ መሥዋዕት አድርጎ ያምጣ፤ እርሱም ስለ ኃጢአት ስርየት የሚቀርብ መሥዋዕት እንጂ የእህል መባ ስላልሆነ የወይራ ዘይት ወይም ዕጣን አይጨምርበት።
እናንተ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ታውቃላችሁ፤ እርሱ ምንም እንኳ ሀብታም ቢሆን በእርሱ ድኻ መሆን እናንተ ሀብታሞች እንድትሆኑ ስለ እናንተ ብሎ ድኻ ሆነ።