ሉቃስ 2:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ በሮማውያን ግዛት ያሉ ሰዎች ሁሉ እንዲቈጠሩ ከሮማው ንጉሠ ነገሥት አውግስጦስ ታወጀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ዘመን፣ የዓለሙ ሁሉ ሕዝብ እንዲቈጠርና እንዲመዘገብ ከአውግስጦስ ቄሳር ትእዛዝ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ወራት የመላው ዓለም ሕዝብ እንዲመዘገቡ ከአውግስጦስ ቄሣር ትእዛዝ ወጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ወራት እንዲህ ሆነ፤ ሰው ሁሉ ይቈጠር ዘንድ ከአውግስጦስ ቄሣር ትእዛዝ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ወራት ዓለሙ ሁሉ እንዲጻፍ ከአውግስጦስ ቄሣር ትእዛዝ ወጣች። |
የሮም ንጉሠ ነገሥት ጢባርዮስ በነገሠ በዐሥራ አምስተኛው ዓመት፥ ጰንጤናዊው ጲላጦስ የይሁዳ ምድር አስተዳዳሪ ነበር፤ ሄሮድስ የገሊላ አገረ ገዢ ነበር፤ እንዲሁም ወንድሙ ፊልጶስ የኢጡርያስና የጥራኮኒዶስ ገዢ፥ ሊሳኒዮስም የአቢሌኔ ገዢ ነበሩ፤
ከእነርሱም አንዱ አጋቦስ የሚባለው ተነሥቶ በዓለም ሁሉ ታላቅ ራብ እንደሚሆን በመንፈስ ቅዱስ አነሣሽነት ትንቢት ተናገረ፤ ይህም የሆነው በሮም ንጉሠ ነገሥት በቀላውዴዎስ ዘመን ነበር።
በደለኛ ከሆንኩ ወይም በሞት የሚያስቀጣ በደል ካደረግሁ ከሞት ልዳን አልልም፤ ነገር ግን የእነርሱ ክስ ከንቱ ከሆነ ማንም ለእነርሱ አሳልፎ ሊሰጠኝ አይችልም፤ እኔ ወደ ሮማ ንጉሠ ነገሥት ይግባኝ ብዬአለሁ።”
እርሱ ግን ጉዳዩ በሮም ንጉሠ ነገሥት እንዲታይለት ፈልጎ ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ይግባኝ በማለቱ ወደ እዚያ እስክልከው ድረስ በእስር ቤት እንዲቈይ አዘዝኩ።”