በዚያም አደባባይ ዕዝራ በቅጽሩ በር አጠገብ ቆሞ ከንጋት እስከ ቀትር የሕጉን መጽሐፍ ከፍ ባለ ድምፅ አነበበላቸው፤ ወንዶችም ሴቶችም ሁሉ በከፍተኛ ስሜት አዳመጡት።
ሉቃስ 19:48 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ሰዎች ሁሉ ኢየሱስን ለመስማት በመፈለግ ልባቸው ተማርኮ ስለ ነበረ ሊገድሉት የፈለጉት ወገኖች ምንም ማድረግ አልቻሉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ሕዝቡ ሁሉ ከርሱ ጋራ ተቈራኝተው ትምህርቱን ይከታተሉ ስለ ነበር፣ የሚያደርጉት ግራ ገባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚያደርጉበትንም አጡ፤ ሕዝቡ ሁሉ በታላቅ ትኩረት ይሰሙት ነበርና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን የሚያደርጉትን አጡ፤ ሕዝቡ ሁሉ ትምህርቱን በመስማት ይመሰጡ ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚያደርጉበትንም አጡ፤ ሕዝቡ ሁሉ ሲሰሙት ተንጠልጥለውበት ነበርና። |
በዚያም አደባባይ ዕዝራ በቅጽሩ በር አጠገብ ቆሞ ከንጋት እስከ ቀትር የሕጉን መጽሐፍ ከፍ ባለ ድምፅ አነበበላቸው፤ ወንዶችም ሴቶችም ሁሉ በከፍተኛ ስሜት አዳመጡት።
አንድ ቀን ኢየሱስ በቤተ መቅደስ ተገኝቶ ሕዝቡን ያስተምርና ወንጌልንም ያበሥር በነበረበት ጊዜ የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ሽማግሌዎችም ወደ እርሱ መጡ፤
ይሰሙን ከነበሩትም ሴቶች አንድዋ የትያጥሮን ከተማ ተወላጅ የሆነች የቀይ ልብስ ነጋዴ፥ ልድያ የምትባል ሴት ነበረች፤ እርስዋ እግዚአብሔርን የምታመልክ ሴት ነበረች፤ ጌታም ልቡናዋን ስለ ከፈተላት ጳውሎስ የሚናገረውን ቃል ታዳምጥ ነበር፤