ሉቃስ 19:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንም ሰው ‘ለምን ትፈቱታላችሁ?’ ብሎ ቢጠይቃችሁ፥ ‘ጌታ ስለሚያስፈልገው ነው’ ብላችሁ መልሱለት።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንም፣ ‘ለምን ትፈቱታላችሁ?’ ብሎ ቢጠይቃችሁ፣ ‘ለጌታ ያስፈልገዋል’ በሉት።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም ‘ስለምን ትፈቱታላችሁ?’ ብሎ ቢጠይቃችሁ፥ እንዲሁ ‘ለጌታ ያስፈልገዋል፤’ በሉ”። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለምን ትፈቱታላችሁ? የሚላችሁ ቢኖር ጌታው ይሻዋል በሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማንም፦ ስለ ምን ትፈቱታላችሁ? ብሎ ቢጠይቃችሁ፥ እንዲሁ፦ ለጌታ ያስፈልገዋል በሉ አላቸው። |
“በፊታችሁ ወደምትገኘው መንደር ሂዱ፤ እዚያም በደረሳችሁ ጊዜ ገና ማንም ሰው ያልተቀመጠበትን የአህያ ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ ወዲህ አምጡት።
እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ቃሉን መላኩ የታወቀ ነው፤ በሁሉ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ሰላምን እየሰበከ የመጣውም ለእነርሱ ነው።