ሉቃስ 18:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጴጥሮስም “እነሆ፥ እኛ ያለንን ሁሉ ትተን ተከትለንሃል” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጴጥሮስም፣ “እነሆ፤ እኛ ያለንን ሁሉ ትተን ተከትለንሃል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጴጥሮስም “እነሆ፥ እኛ ሁሉን ትተን ተከተለንሃል፤” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጴጥሮስም፥ “እነሆ፥ እኛ ሁሉን ትተን ተከትለንሃል፤ እንግዲህ ምን እናገኛለን?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጴጥሮስም፦ እነሆ፥ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ አለ። |
ኢየሱስ ከዚያ ቦታ ተነሥቶ ሲሄድ ሳለ ማቴዎስ የተባለውን ቀራጭ በቀረጥ መቀበያ ስፍራ ተቀምጦ አየውና “ተከተለኝ!” አለው፤ እርሱም ተነሥቶ ተከተለው።
እንግዲህ ከዚህ በፊት ጠቃሚዎች ናቸው ብዬ አምንባቸው የነበሩትን ነገሮች ሁሉ ስለ ክርስቶስ ብዬ ዋጋ እንደሌላቸው ከንቱ ነገሮች አድርጌ እቈጥራቸዋለሁ።