ሉቃስ 18:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእውነት እላችኋለሁ! የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን ያልተቀበላት ሰው አይገባባትም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እውነት እላችኋለሁ፤ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበል ሁሉ ከቶ አይገባባትም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እውነት እላችኋለሁ፤ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበላት ሁሉ ከቶ አይገባባትም፤” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እውነት እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃናት ያልተቀበላት አይገባባትም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እውነት እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበላት ሁሉ ከቶ አይገባባትም አለ። |
ኢየሱስ ግን ሕፃናትን ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አለ፤ “የእግዚአብሔር መንግሥት እንደእነዚህ ላሉት ስለ ሆነች ሕፃናት ወደ እኔ ይምጡ፤ አትከልክሉአቸው።