ስለ ሕያዋን ፍጥረት ሁሉ በእግዚአብሔር መጽሐፍ የተጻፈውን ፈልጋችሁ አንብቡ፤ ከእነዚህ ፍጥረቶች አንዱ እንኳ አይጠፋም፤ የኑሮ ጓደኛ አጥቶ ብቻውን የሚኖርም አይገኝም፤ እግዚአብሔር ራሱ ይህ እንዲሆን ስላዘዘ እርሱ ራሱ በኅብረት እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል።
ሉቃስ 16:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አብርሃም ግን ‘ለእነርሱ የሙሴና የነቢያት መጻሕፍት አሉላቸው፤ እነርሱን ይስሙ’ አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አብርሃም ግን፣ ‘ሙሴና ነቢያት አሏቸው፤ እነርሱን ይስሙ’ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃም ግን ‘ሙሴና ነቢያት አሉላቸው፤ እነርሱን ይስሙ፤’ አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም፦ ‘ሙሴና ነቢያት አሉአቸው፤ እነርሱን ይስሙ’ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃም ግን፦ ሙሴና ነቢያት አሉአቸው፤ እነርሱን ይስሙ አለው። |
ስለ ሕያዋን ፍጥረት ሁሉ በእግዚአብሔር መጽሐፍ የተጻፈውን ፈልጋችሁ አንብቡ፤ ከእነዚህ ፍጥረቶች አንዱ እንኳ አይጠፋም፤ የኑሮ ጓደኛ አጥቶ ብቻውን የሚኖርም አይገኝም፤ እግዚአብሔር ራሱ ይህ እንዲሆን ስላዘዘ እርሱ ራሱ በኅብረት እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል።
እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ይላል፦ “በየጐዳናው ቆማችሁ ተመልከቱ፤ ጥንታዊና መልካም የሆነችው መንገድ የትኛዋ እንደ ሆነች ጠይቃችሁ ተረዱ፤ ባገኛችኋትም ጊዜ በእርስዋ ሂዱ፤ በሰላምም ትኖራላችሁ።” ሕዝቡ ግን “በእርስዋ አንሄድም!” አሉ።
ኢየሱስ ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፦ “የሕግና የነቢያት መጻሕፍት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ ሲነገሩ ቈይተው ነበር፤ ከዚያም ወዲህ የሚነገረው የእግዚአብሔር መንግሥት የምሥራች ቃል ነው፤ እያንዳንዱም ሰው ወደዚያች መንግሥት ለመግባት ብርቱ ጥረት ያደርጋል።