መርዶክዮስም ሰማያዊና ነጭ ልብሰ መንግሥት ለብሶ፥ ሐምራዊ ካባ ደርቦና ውብ የሆነ የወርቅ አክሊል ደፍቶ ከቤተ መንግሥት ብቅ አለ፤ በሱሳም ከተማ የሆታና የእልልታ ድምፅ አስተጋባ።
ሉቃስ 16:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ቀይ ከፋይና ቀጭን ልብስ የሚለብስ አንድ ሀብታም ሰው ነበር፤ እርሱም በየቀኑ በቅንጦት ይኖር ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “ሐምራዊና ቀጭን በፍታ የለበሰ፣ በየቀኑም በተድላ ደስታ የሚኖር አንድ ሀብታም ሰው ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በሐምራዊና በክት ልብስ የሚሽቀረቀር አንድ ሀብታም ሰው ነበረ፤ ዕለት ዕለትም እየተመቸው በቅንጦት ይኖር ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አንድ ባለጸጋ ሰው ነበረ፤ ቀይ ሐርና ነጭ ሐር፥ እጅግም ቀጭን ልብስ ይለብስ ነበር፤ ዘወትርም ተድላና ደስታ ያደርግ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀይ ልብስና ቀጭን የተልባ እግር የለበሰ አንድ ባለ ጠጋ ሰው ነበረ፥ ዕለት ዕለትም እየተመቸው በደስታ ይኖር ነበር። |
መርዶክዮስም ሰማያዊና ነጭ ልብሰ መንግሥት ለብሶ፥ ሐምራዊ ካባ ደርቦና ውብ የሆነ የወርቅ አክሊል ደፍቶ ከቤተ መንግሥት ብቅ አለ፤ በሱሳም ከተማ የሆታና የእልልታ ድምፅ አስተጋባ።
ከብርና ከወርቅ የተሠሩ ብዙ ጌጣጌጦች ነበሩሽ፤ ከልዩ ልዩ ሐር የተሠሩና በጥልፍ ጌጥ የተዋቡ ውድ ልብሶች ነበሩሽ፤ ምርጥ ከሆነ ዱቄት የተጋገረ ዳቦ፥ ማርና የወይራ ዘይት ትመገቢ ነበር፤ ውበትሽ እጅግ እየጨመረ ስለ ሄደ ንግሥት ለመሆን በቃሽ።
የእኅትሽ የሰዶም በደል ይህ ነው፤ እርስዋና መንደሮችዋ ኲራት ተሰምቶአቸው ነበር። የተትረፈረፈ ምግብና የተዝናና ኑሮ ቢኖራቸውም ችግረኞችንና ድኾችን አይረዱም ነበር።
የመርከብ ሸራሽ እንደ ዓላማ ሆኖ ከሩቅ ይታይ ዘንድ፥ በእጅ ሥራ ባጌጠ የግብጽ በፍታ ተሠርቶአል፤ መጋረጃዎችሽ ከቆጵሮስ ደሴት በተገኘ እጅግ በሚያምር ሰማያዊ ሐምራዊ ጨርቅ ተሠርቶአል፤
ደግሞም ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፤ “አንድ ሀብታም ሰው ቤቱን የሚያስተዳድርለት መጋቢ ነበረው፤ ሰዎች ‘ይህ መጋቢ ንብረትህን ያባክናል’ ብለው ለሀብታሙ ሰው ከሰሱት።
ሴቲቱ ሐምራዊና ቀይ ልብስ ለብሳ ነበር፤ በወርቅና በከበረ ድንጋይ በዕንቆችም አሸብርቃ ነበር፤ በእጅዋም የሚያጸይፍ ነገርና የአመንዝራነትዋ ርኲሰት የሞላበትን የወርቅ ጽዋ ይዛ ነበር።
“ቀጭን ልብስና ሐምራዊ ልብስ ቀይ ልብስም ትለብስ የነበረች፥ በወርቅና በከበረ ድንጋይ በዕንቊም ታሸበርቅ የነበረች፤ ታላቂቱ ከተማ ወዮላት! ወዮላት!
እርስዋ ለራስዋ ክብርንና ምቾትን የሰጠችውን ያኽል ሥቃይና ሐዘን ስጡአት፤ እርስዋ በልብዋ ‘እንደ ንግሥት ተቀምጬአለሁ፤ መበለትም አይደለሁም፤ ሐዘንም ከቶ አይደርስብኝም’ በማለት ትመካለች።
ጌዴዎን የተቀበለው የጆሮ ጒትቻ ኻያ ኪሎ ያኽል የሚመዝን ሆነ፤ ይህም ሌላውን ጌጣጌጥ፥ የአንገት ሐብልና የምድያማውያን ነገሥታት ይለብሱት የነበረውን ሐምራዊ ልብስ፥ እንዲሁም በግመሎቻቸው አንገት ዙሪያ ያለውን ጌጥ ሳይጨምር ነው።