ሉቃስ 14:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህ ዐይነቱ ጨው ለእርሻ መሬትም ሆነ ለማዳበሪያ የማይጠቅም ስለ ሆነ ወዲያ አውጥተው ይጥሉታል፤ ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ!” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመሬትም ሆነ ለማዳበሪያነት የማይጠቅም በመሆኑ ወደ ውጭ ይጣላል። “ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለምድርም ሆነ ለፍግ መቈለያ አይጠቅምም፤ ወደ ውጭም ይጥሉታል። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለምድርም ቢሆን፥ ለፍግ መቆለያም ቢሆን አይረባም፤ ነገር ግን ወደ ውጭ ይጥሉታል፤ የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለምድር ቢሆን ለፍግ መቈለያም ቢሆን አይረባም፤ ወደ ውጭ ይጥሉታል። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ። |
ሌላው ዘር ግን በመልካም መሬት ላይ ወድቆ በቀለ፤ ቡቃያውም አድጎ እያንዳንዱ መቶ እጥፍ አፈራ።” ቀጥሎም ኢየሱስ “ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ!” አለ።
“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ! ድል ለሚነሣ ከተሰወረው መና እሰጠዋለሁ፤ አዲስ ስም የተጻፈበትን ነጭ ድንጋይም እሰጠዋለሁ፤ ከተቀባዩ በቀር ይህን ሌላ ማንም አያውቀውም።
“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ! ‘ድል ለሚነሣ በእግዚአብሔር ገነት ውስጥ ካለው ከሕይወት ዛፍ ፍሬ እንዲበላ አደርገዋለሁ።’