“እነሆ፥ አሁን ወደ ኢየሩሳሌም መሄዳችን ነው፤ በዚያም የሰው ልጅ ለካህናት አለቆችና ለሕግ መምህራን ተላልፎ ይሰጣል፤ እነርሱም የሞት ፍርድ ይፈርዱበታል።
ሉቃስ 13:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ ዛሬና ነገ ከነገ ወዲያም መንገዴን ወደ ኢየሩሳሌም መቀጠል አለብኝ፤ ነቢይ ከኢየሩሳሌም በቀር በሌላ ቦታ መሞት አይገባውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ ነቢይ ከኢየሩሳሌም ውጭ ይሞት ዘንድ አይገባምና ዛሬና ነገ፣ ከነገ ወዲያም ወደዚያው ጕዞዬን እቀጥላለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳሩ ግን ነቢይ ከኢየሩሳሌም ውጭ ሊጠፋ አይገባውምና ዛሬና ነገ ከነገ በስቲያም መሄድ ያስፈልገኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛሬና ነገስ አለሁ፤ በሦስተኛው ቀን ግን እሄዳለሁ፤ ነቢይ በኢየሩሳሌም እንጂ በውጭ ሊሞት አይገባውምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳሩ ግን ነቢይ ከኢየሩሳሌም ውጭ ይጠፋ ዘንድ አይገባውምና ዛሬና ነገ ከነገ በስቲያም ልሄድ ያስፈልገኛል። |
“እነሆ፥ አሁን ወደ ኢየሩሳሌም መሄዳችን ነው፤ በዚያም የሰው ልጅ ለካህናት አለቆችና ለሕግ መምህራን ተላልፎ ይሰጣል፤ እነርሱም የሞት ፍርድ ይፈርዱበታል።
ከዚያን ወዲያ ኢየሱስ በአይሁድ መካከል በግልጥ አልተመላለሰም፤ ነገር ግን ከዚያ ወጥቶ በበረሓ አጠገብ ወዳለችው ኤፍሬም ወደምትባለው ከተማ ሄደ፤ እዚያ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ቈየ።
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “በቀን ውስጥ ያለው ጊዜ ዐሥራ ሁለት ሰዓት አይደለምን? በቀን የሚመላለስ የዚህን ዓለም ብርሃን ስለሚያይ አይሰናከልም።
ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “አሁን ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ብርሃን አለ፤ ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማ የሚመላለስ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።
“ደግሞም እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ እንደ ቀባውና ኀይልም እንደ ሰጠው ታውቃላችሁ፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ እርሱን መልካም ነገርን እያደረገና በዲያብሎስ የተያዙትን ሁሉ እየፈወሰ ተዘዋወረ።
በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎችና አለቆቻቸው ኢየሱስ አዳኝ መሆኑን አላወቁም፤ በየሰንበቱም የሚነበቡትን የነቢያት መጻሕፍት ባለማስተዋላቸው በእርሱ ላይ በፈረዱበት ጊዜ ትንቢቱ ተፈጻሚ እንዲሆን አድርገዋል።