አክዓብም “የይምላ ልጅ የሆነ ሚክያስ የተባለ ሌላ ነቢይም አለ፤ ነገር ግን እኔ እርሱን አልወደውም፤ እርሱ ምን ጊዜም ቢሆን ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም የትንቢት ቃል አይናገርም!” ሲል መለሰለት። ኢዮሣፍጥም “ይህን ማለት አይገባህም!” አለው።
ሉቃስ 11:45 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሕግ መምህራኑም አንዱ ኢየሱስን፥ “መምህር ሆይ፥ ይህንን ስትል እኛንም መስደብህ ነው!” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሕግ ዐዋቂዎች አንዱ መልሶ “መምህር ሆይ፤ እንዲህ ስትናገር እኮ እኛንም መስደብህ ነው” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሕግ አዋቂዎችም አንዱ መልሶ፦ “መምህር ሆይ! ይህን ስትል እኮ እኛን ደግሞ መስደብህ ነው፤” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሕግ ዐዋቂዎችም አንዱ መልሶ፥ “መምህር ሆይ፥ ይህን ስትል እኛን እኮ መስደብህ ነው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሕግ አዋቂዎችም አንዱ መልሶ፦ መምህር ሆይ፥ ይህን ማለትህ እኛን ደግሞ መስደብህ ነው አለው። |
አክዓብም “የይምላ ልጅ የሆነ ሚክያስ የተባለ ሌላ ነቢይም አለ፤ ነገር ግን እኔ እርሱን አልወደውም፤ እርሱ ምን ጊዜም ቢሆን ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም የትንቢት ቃል አይናገርም!” ሲል መለሰለት። ኢዮሣፍጥም “ይህን ማለት አይገባህም!” አለው።
እኔ በምናገርበት ጊዜ ሁሉ የምናገረው ዐመፅንና ጥፋትን ነው፤ አምላክ ሆይ! አንተ ያዘዝከኝን የትንቢት ቃል በመናገሬ፥ እኔ ዘወትር እሰደባለሁ፤ መላገጫም ሆኛለሁ።
እኔም መልሼ እንዲህ አልኩ፦ “እኔ ብነግራቸውና ባስጠነቅቃቸው ማን ሊሰማኝ ይችላል? እነርሱ እልኸኞች ስለ ሆኑ፥ ቃልህን መስማት አይፈልጉም፤ የአንተን ቃል ስነግራቸው በንቀት መሳቂያ ያደርጉኛል።
ኢየሱስም እንዲህ አለ፦ “እናንተም የሕግ መምህራን ወዮላችሁ! በሰው ላይ ከባድ ሸክም ትጭናላችሁ፤ እናንተ ግን ሸክሙን በጣታችሁ እንኳ አትነኩትም።
“እናንተ የሕግ መምህራን ወዮላችሁ! የዕውቀት በር መክፈቻ የሆነውን የእውነት ቊልፍ ይዛችኋል፤ ነገር ግን እናንተ ራሳችሁ አልገባችሁበትም፤ መግባት የሚፈልጉትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።”