La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 10:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ሲወርድ በመንገድ ላይ ሳለ ቀማኞች አግኝተውት ልብሱን ገፈፉት፤ ከደበደቡትም በኋላ ሊሞት ሲያጣጥር ጥለውት ሄዱ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢየሱስም እንዲህ ሲል መልስ ሰጠው፤ “አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ሲወርድ በወንበዴዎች እጅ ወደቀ፤ ልብሱንም ገፍፈው ደበደቡት፤ በሞት አፋፍ ላይ ጥለውት ሄዱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፦ “አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ፤ በወንበዴዎችም እጅ ወደቀ፤ እነርሱም ደግሞ ገፈፉት፤ ደበደቡትም፤ በሕይወትና በሞት መካከልም ትተውት ሄዱ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “አንድ ሰው ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ኢያ​ሪኮ ይወ​ርድ ነበር፤ ሽፍ​ቶ​ችም አገ​ኙት፤ ደበ​ደ​ቡት፥ አቈ​ሰ​ሉት፥ ልብ​ሱ​ንም ገፍ​ፈው፤ በሕ​ይ​ወ​ትና በሞት መካ​ከል ጥለ​ውት ሄዱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፦ አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ በወንበዴዎችም እጅ ወደቀ፤ እነርሱም ደግሞ ገፈፉት ደበደቡትም በሕይወትና በሞት መካከልም ትተውት ሄዱ።

Ver Capítulo



ሉቃስ 10:30
7 Referencias Cruzadas  

ሞተው ወደ መቃብር ከሚወርዱት ሰዎች ጋር ተቈጥሬአለሁ፤ ምንም ረዳት እንደሌለው ሰው ሆኜአለሁ።


እኔ እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው። በባቢሎን ጣዖቶች ላይ የምፈርድበትና በሀገሪቱም የሚገኙ ቊስለኞች የጭንቀት ድምፅ የሚያሰሙበት ጊዜ ይመጣል፤


በጦር ሜዳ እንደ ቈሰለ ወታደር በከተማው መንገዶች እየተዝለፈለፉ በእናታቸው ክንድ ላይ ሆነው፥ “ምግብና ውሃ!” እያሉ እያለቀሱ፥ ሕይወታቸው ያልፋል።


በዚህም ዐይነት የባቢሎንን ንጉሥ ኀይል በማጠንከር የእኔን ሰይፍ በእጁ አስይዘዋለሁ። የግብጽን ንጉሥ ኀይል ግን እሰብራለሁ፤ እርሱም ለሞት የሚያደርስ ቊስል እንደ ደረሰበት ሰው በጠላቱ ፊት ይቃትታል።


እንደ አጋጣሚ አንድ ካህን በዚያ መንገድ ይሄድ ነበር፤ ተደብድቦ የተጣለውን ሰው ባየው ጊዜ ምንም ሳያደርግለት በሌላ በኩል አልፎ ሄደ።


ኢየሱስ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ አቅርቦ እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ! ወደ ኢየሩሳሌም መሄዳችን ነው፤ ስለ ሰው ልጅ በነቢያት የተጻፈው ሁሉ በዚያ ይፈጸማል።


ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ከተናገረ በኋላ ጒዞውን ወደ ኢየሩሳሌም በመቀጠል፥ ከደቀ መዛሙርቱ ፊት ፊት ይሄድ ነበር።