ሉቃስ 1:39 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ማርያም በተራራማው በይሁዳ አገር ወዳለችው ከተማ በፍጥነት ተነሥታ ሄደች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማርያምም በዚያው ሰሞን በፍጥነት ተነሥታ ወደ ደጋው አገር፣ ወደ አንድ የይሁዳ ከተማ ሄደች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማርያምም በእነዚያ ቀናት ተነሥታ ወደ ተራራማው አገር በይሁዳ ወደምትገኝ ከተማ ፈጥና ሄደች፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ወራት ማርያም ፈጥና ተነሣች፤ ወደ ተራራማው ሀገር ወደ ይሁዳ ከተማም ደረሰች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማርያምም በዚያ ወራት ተነሥታ ወደ ተራራማው አገር ወደ ይሁዳ ከተማ ፈጥና ወጣች፥ |
በዚህ ዐይነት ኢያሱ ምድሪቱን በሙሉ፥ የተራራማውን አገር፥ ኔጌብን፥ የተራራውን ቊልቊለትና ነገሥታቱን ሁሉ ያዘ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ሁሉንም ፈጀ እንጂ አንድ ሰው እንኳ በሕይወት እንዲኖር አላስተረፈም።
ስለዚህም የንፍታሌም ይዞታ በሆነችው በኮረብታማዋ ምድር በምትገኘው በገሊላ፥ ቄዴሽ ተብላ የምትጠራውን፥ በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ሴኬምንና በኮረብታማው በይሁዳ ምድር ኬብሮን የምትባለው ቂርያት አርባቅን መርጠው ለዩ፤