የክህነት ሹመታችሁን ሥርዓት ለመፈጸም ሰባት ቀን ስለሚወስድ ይኸው ሥርዓት እስከሚፈጸምበት እስከ ሰባት ቀን ድረስ ከመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አትወጡም።
ዘሌዋውያን 8:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአታችሁን ለማስወገድ ይህን ዛሬ ያደረግነውን ሥርዓት እንድንፈጽም እግዚአብሔር አዞናል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዛሬ የተፈጸመው ይህ ሥርዐት ለእናንተ ማስተስረያ እግዚአብሔር ያዘዘው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዛሬ እንደተደረገው እንዲሁ ለእናንተ ማስተስረያም እንዲደረግ ጌታ አዝዞአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህ ቀን እንደ ተደረገ ለእናንተ ለማስተስረያ ይደረግ ዘንድ እንዲሁ እግዚአብሔር አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚህ ቀን እንደ ተደረገ ለእናንተ ለማስተስረያ ይደረግ ዘንድ እንዲሁ እግዚአብሔር አዘዘ። |
የክህነት ሹመታችሁን ሥርዓት ለመፈጸም ሰባት ቀን ስለሚወስድ ይኸው ሥርዓት እስከሚፈጸምበት እስከ ሰባት ቀን ድረስ ከመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አትወጡም።
ስለዚህም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ በመፈጸም ሰባት ቀን ሙሉ ሌሊትና ቀን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ትቈያላችሁ፤ ይህን ባታደርጉ ግን ትሞታላችሁ፤ ይህ እግዚአብሔር ያዘዘኝ ሕግ ነው።”
እርሱ እንደ ሌሎቹ የካህናት አለቆች በመጀመሪያ ስለ ራሱ ኃጢአት፥ በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት በየቀኑ መሥዋዕት ማቅረብ አያስፈልገውም፤ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ባቀረበ ጊዜ ይህን ነገር በማያዳግም ሁኔታ ፈጽሞታል።