በዚህም ሁኔታ ኀምሳኛውን ዓመት ለይታችሁ በምድሪቱ ለሚኖሩት ሁሉ ነጻነትን ታውጃላችሁ፤ ከዚያ በፊት የተሸጠ ማናቸውም መሬት ለባለቤቱ ወይም ለዘሩ ይመለሳል፤ ባርያም ሆኖ ለማገልገል የተሸጠ ሰው ወደ ቤተሰቡ ይመለሳል።
ዘሌዋውያን 27:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሬቱን የኢዮቤልዩ ዓመት እንዳለፈ ወዲያውኑ ለይቶ የሰጠ ከሆነ ሙሉውን ዋጋ መክፈል ይኖርበታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውየው ዕርሻውን የቀደሰው በኢዮቤልዩ ዓመት ከሆነ፣ የተወሰነው ዋጋ አይለወጥም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሻውንም ከኢዮቤልዩ ዓመት ጀምሮ ቢቀድስ፥ እንደ ግምትህ መጠን ይጸናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሻውንም ከኢዮቤልዩ ዓመት ጀምሮ ቢሳል፥ እንደ ግምቱ መጠን ይቆማል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሻውንም ከኢዮቤልዩ ዓመት ጀምሮ ቢቀድስ፥ እንደ ግምቱ መጠን ይቆማል። |
በዚህም ሁኔታ ኀምሳኛውን ዓመት ለይታችሁ በምድሪቱ ለሚኖሩት ሁሉ ነጻነትን ታውጃላችሁ፤ ከዚያ በፊት የተሸጠ ማናቸውም መሬት ለባለቤቱ ወይም ለዘሩ ይመለሳል፤ ባርያም ሆኖ ለማገልገል የተሸጠ ሰው ወደ ቤተሰቡ ይመለሳል።
“አንድ ሰው ቤቱን ለእግዚአብሔር የተለየ ስጦታ አድርጎ ሲያቀርብ ካህኑ የቤቱን መልካምነትና መጥፎነት ገምቶ ዋጋውን ይወስን፤ ያም ዋጋ የመጨረሻ ይሆናል።
“አንድ ሰው ከመሬቱ ከፍሎ ለእግዚአብሔር የተለየ ስጦታ አድርጎ ቢያቀርብ፥ ዋጋው መሬቱ በሚቀበለው ዘር መጠን ይወሰን፤ ይኸውም ለእያንዳንዱ ኪሎ ግራም ገብስ ተቀባይ መሬት ኀምሳ ጥሬ ብር ይክፈል።
መሬቱን የሰጠው የኢዮቤልዩ ዓመት ካለፈ ዘግይቶ ከሆነ ግን ካህኑ እስከ ተከታዩ የኢዮቤልዩ ዓመት ያለውን ቀሪ ጊዜ በመገመት ዋጋው እንዲቀነስ ያድርግ።