እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፥ ይህ ሕዝብ ክህነትን፥ የክህነትን ሥርዓትንና አንተ ከካህናትና ከሌዋውያን ጋር ያደረግኸውን ቃል ኪዳን እንዴት እንዳረከሰ ተመልከት!
ዘሌዋውያን 21:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን የአካል ጒድለት ስላለበት ወደተቀደሰው መጋረጃ ወይም ወደ መሠዊያው አይቅረብ፤ እነዚህን ለእኔ የተቀደሱትን ነገሮች ማርከስ የለበትም፤ እነርሱንም የቀደስኳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’ ” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እንከን ያለበት ስለ ሆነ መቅደሴን እንዳያረክስ ወደ መጋረጃው አይቅረብ ወይም ወደ መሠዊያው አይጠጋ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ነውረኛ ነውና መቅደሶቼን እንዳያረክስ ወደ መጋረጃው አይግባ፥ ወደ መሠዊያውም አይቅረብ፤ የምቀድሳቸው እኔ ጌታ ነኝና።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ነውረኛ ነውና መቅደሶችን እንዳያረክስ ወደ መጋረጃው አይግባ፤ ወደ መሠዊያውም አይቅረብ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝና።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ነውረኛ ነውና መቅደሶቼን እንዳያረክስ ወደ መጋረጃው አይግባ፥ ወደ መሠዊያውም አይቅረብ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፥ ይህ ሕዝብ ክህነትን፥ የክህነትን ሥርዓትንና አንተ ከካህናትና ከሌዋውያን ጋር ያደረግኸውን ቃል ኪዳን እንዴት እንዳረከሰ ተመልከት!
የሚቃጠል መሥዋዕትና የምግብ መባ ለእኔ ለአምላካቸው የሚያቀርቡ ካህናት ለእኔ የተለዩና ስሜንም የማያረክሱ መሆን አለባቸው፤ ስለዚህ የተቀደሱ ይሆናሉ።
ይኸውም መብላት ለማይፈቀድለት ሰው ቢሰጡት በደል ሆኖ በዚያ ሰው ላይ ቅጣት ያስከትልበታል፤ ስጦታዎችን ሁሉ የምቀድስ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”