ዘሌዋውያን 19:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ምድሪቱ በዝሙትና በርኲሰት እንዳትሞላ ታመነዝር ዘንድ ለሴት ልጅህ አትፍቀድላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ምድሪቱ ወደ ግልሙትና አዘንብላ በርኩሰት እንዳትሞላ፣ ሴት ልጅህ ጋለሞታ ትሆን ዘንድ አታዋርዳት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ምድሪቱ እንዳታመነዝር በበርኩስነትም እንዳትሞላ ሴት ልጅህን እንድታመነዝር አድርገሃት አታርክሳት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ምድሪቱ ከግልሙትና፥ ከርኵሰትም እንዳትሞላ ሴት ልጅህን ታመነዝር ዘንድ አታርክሳት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድሪቱ ከግልሙትና ከርኩሰትም እንዳትሞላ ሴት ልጅህን ታመነዝር ዘንድ አታርክሳት። |
ካህናት ለአምላካቸው ተለይተው የተቀደሱ ስለ ሆኑ፥ አመንዝራ የነበረች ሴት፥ ወይም ክብረ ንጽሕናዋ የተደፈረ ልጃገረድ ወይም አግብታ የፈታች ሴት አያግቡ፤
ሰውነታችሁ የክርስቶስ አካል ክፍል መሆኑን ታውቁ የለምን? ታዲያ፥ የክርስቶስን አካል ክፍል ወስጄ የአመንዝራ ሴት አካል ክፍል እንዲሆን ላደርገው ይገባልን? ከቶ አይገባም!
በአባትዋ ቤት እያለች አሳፋሪ የሆነውን የዝሙት ሥራ በእስራኤል መካከል ስለ ሠራች ወደ አባትዋ ቤት ደጃፍ ይውሰዱአት፤ በዚያም እርስዋ የምትኖርበት ከተማ ሰዎች በድንጋይ ወግረው ይግደሉአት፤ በዚህም ዐይነት ይህን ክፉ ነገር ከመካከላችሁ አስወግዱ።