ዘሌዋውያን 18:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኅጎቼን ፈጽሙ፤ ሥርዓቴን ጠብቁ። እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕጌን ታዘዙ፤ ሥርዐቴንም በጥንቃቄ ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍርዴን ፈጽሙ፥ ሥርዓቴንም ጠብቁ፥ በእነርሱም ተመላለሱ፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍርዴን አድርጉ፤ በእርስዋም ትሄዱ ዘንድ ሥርዐቴን ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍርዴን አድርጉ፥ በእርስዋም ትሄዱ ዘንድ ሥርዓቴን ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። |
“ትእዛዞቼን ጠብቁ፤ አንዱን እንስሳ ከሌላው ጋር አታዳቅል፥ በአንድ እርሻ ላይ ሁለት ዐይነት እህል አትዝራ፥ ከሁለት ዐይነት ነገር ተፈትሎ የተሠራ ልብስ አትልበስ።
“አሁን ተሻግራችሁ በርስትነት በሚሰጣችሁ ምድር እንድትጠብቁት እግዚአብሔር አምላክህ እንዳስተምርህ ያዘዘኝ ትእዛዞች፥ ሕግና ሥርዓት እነዚህ ናቸው።