“የመንጻትዋም ወራት በተፈጸመ ጊዜ ስለ ወንድ ልጅም ሆነ ስለ ሴት ልጅ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብ የአንድ ዓመት የበግ ጠቦትና ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚሆን ርግብ ወይም ዋኖስ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ አምጥታ በዚያ ለሚያገለግለው ካህን ትስጠው።
ዘሌዋውያን 15:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በስምንተኛውም ቀን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች አምጥታ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ለካህኑ ትስጥ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በስምንተኛውም ቀን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት የዋኖስ ጫጩቶች ይዛ በመቅረብ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ለካህኑ ትሰጣለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በስምንተኛውም ቀን ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ይዛ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ታመጣቸዋለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በስምንተኛውም ቀን ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ይዛ ወደ ካህኑ ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ታመጣቸዋለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስምንተኛውም ቀን ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ይዛ ወደ ካህኑ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ታመጣቸዋለች። |
“የመንጻትዋም ወራት በተፈጸመ ጊዜ ስለ ወንድ ልጅም ሆነ ስለ ሴት ልጅ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብ የአንድ ዓመት የበግ ጠቦትና ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚሆን ርግብ ወይም ዋኖስ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ አምጥታ በዚያ ለሚያገለግለው ካህን ትስጠው።
“ሴትዮዋ የበግ ጠቦት ማምጣት ካልቻለች፥ ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ታምጣ፤ እነርሱም አንዱ ለሚቃጠል መሥዋዕት ሌላውም ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ይቀርባሉ፤ ካህኑም ያስተሰርይላትና ትነጻለች፤ ከዚያም በኋላ የነጻች ትሆናለች።”
ካህኑም አንዱን ኃጢአት የሚሰረይበት መሥዋዕት፥ ሁለተኛውንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል፤ በዚህም ዐይነት ካህኑ ስለሚፈሰው ርኲሰት በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይላታል፥
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ በዚያም የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሰዎች ሁሉ አስወጣ። የገንዘብ ለዋጮችን ጠረጴዛዎችና የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠ።