ስለዚህም ንዕማን የእግዚአብሔር ሰው ባዘዘው መሠረት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ወርዶ ሰባት ጊዜ በመነከር ታጠበ፤ ከበሽታውም ፈጽሞ ነጻ፤ ሥጋውም እንደ ትንሽ ልጅ ገላ በመታደስ ፍጹም ጤናማ ሆነ፤
ዘሌዋውያን 14:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑም ከሰፈር ወደ ውጪ አውጥቶ ይመርምረው፤ በሽታው የተፈወሰ ከሆነ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑ ከሰፈር ወደ ውጭ ወጥቶ ይመርምረው፤ ሰውየው ከተላላፊ የቈዳ በሽታው ተፈውሶ ከሆነ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም ከሰፈር ወደ ውጭ ይወጣል፤ ካህኑም ያያል፤ እነሆም፥ የለምጹ ደዌ ለምጽ ካለበት ሰው ላይ ቢጠፋ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም ከሰፈር ወደ ውጭ ይወጣል፤ ካህኑም ያየዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም ከሰፈር ወደ ውጭ ይወጣል፤ ካህኑም ያያል፤ እነሆም፥ የለምጹ ደዌ ከለምጻሙ ላይ ቢጠፋ፥ |
ስለዚህም ንዕማን የእግዚአብሔር ሰው ባዘዘው መሠረት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ወርዶ ሰባት ጊዜ በመነከር ታጠበ፤ ከበሽታውም ፈጽሞ ነጻ፤ ሥጋውም እንደ ትንሽ ልጅ ገላ በመታደስ ፍጹም ጤናማ ሆነ፤
አንድ ቀን እመቤትዋን፥ “ጌታዬ ንዕማን በሰማርያ ወደሚገኘው ነቢይ ቢሄድ መልካም ይመስለኛል! ነቢዩ ከዚህ የቆዳ በሽታው ሊያነጻው ይችላል!” አለቻት።
እንዲህም አላቸው፤ “በጥሞና ትእዛዞቼን ብታዳምጡና በፊቴ መልካም የሆነውን ነገር በታዛዥነት ብታደርጉ፥ ኅጎቼንም ሁሉ ብትጠበቁ፥ በግብጻውያን ላይ ካመጣሁባቸው በሽታዎች በአንዱ እንኳ አልቀጣችሁም፤ ፈዋሻችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
“ማንም ሰው በሰውነቱ ላይ እባጭ ወይም ሽፍታ ወይም ቋቊቻ ቢታይና በገላው ላይ የሥጋ ደዌ ቢመስል፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ካህናት ከሆኑት ከልጆቹ ወደ አንዱ ያምጡት።
“ቤቱ እንደገና ታድሶ ከተለሰነ በኋላ ካህኑ መጥቶ በሚመለከትበት ጊዜ ሻጋታው የመስፋፋት ምልክት የማያሳይ ሆኖ ከተገኘ ግን የሻጋታው ምልክት ጨርሶ ስለ ጠፋ ያ ቤት ንጹሕ መሆኑን ካህኑ ያስታውቅ።
እንዲሁም በነቢዩ በኤልሳዕ ጊዜ ብዙ ለምጻሞች በእስራኤል አገር ነበሩ፤ ነገር ግን ከሶርያዊው ከንዕማን በቀር፥ ከእነርሱ አንድ እንኳ አልነጻም።”
ኢየሱስ መልእክተኞቹን እንዲህ አላቸው፦ “ተመልሳችሁ ሂዱና ለዮሐንስ ያያችሁትንና የሰማችሁትን ንገሩት፤ እነሆ፥ ዕውሮች ያያሉ፤ አንካሶች ቀጥ ብለው ይሄዳሉ፤ ለምጻሞች ይነጻሉ፤ ደንቆሮዎች ይሰማሉ፤ ሙታን ይነሣሉ፤ ለድኾችም ወንጌል ይሰበካል።