Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 4:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 እንዲሁም በነቢዩ በኤልሳዕ ጊዜ ብዙ ለምጻሞች በእስራኤል አገር ነበሩ፤ ነገር ግን ከሶርያዊው ከንዕማን በቀር፥ ከእነርሱ አንድ እንኳ አልነጻም።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 በነቢዩ በኤልሳዕ ዘመንም በእስራኤል ብዙ ለምጻሞች ነበሩ፤ ነገር ግን ከሶርያዊው ከንዕማን በቀር ከእነዚያ መካከል ማንም አልነጻም።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 በነቢዩ በኤልሳዕ ዘመንም በእስራኤል ብዙ ለምጻሞች ነበሩ፤ ነገር ግን ከሶርያዊው ከንዕማን በቀር ከእነርሱ ማንም አልነጻም።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 በነ​ቢዩ በኤ​ል​ሳዕ ዘመ​ንም ብዙ ለም​ጻ​ሞች በእ​ስ​ራ​ኤል ውስጥ ነበሩ፤ ነገር ግን ከሶ​ር​ያ​ዊው ከን​ዕ​ማን በቀር ከእ​ነ​ዚያ አንድ እን​ኳን አል​ነ​ጻም።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 በነቢዩ በኤልሳዕ ዘመንም በእስራኤል ብዙ ለምጻሞች ነበሩ፥ ከሶርያዊው ከንዕማን በቀር ከእነርሱ አንድ ስንኳ አልነጻም።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 4:27
10 Referencias Cruzadas  

እኔ አብሬአቸው በነበርኩ ጊዜ በሰጠኸኝ ስምህ ጠብቄአቸዋለሁ፤ እኔ ጠበቅኋቸው፤ ስለዚህ የቅዱስ መጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ከዚያ ከጥፋት ልጅ በቀር ከቶ ከእነርሱ ማንም አልጠፋም።


እርሱ ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ ከካህናት በስተቀር እርሱም ሆነ አብረውት የነበሩት ሰዎች ሊበሉት ያልተፈቀደውን፥ የተቀደሰ ኅብስት በላ።


በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ ዘንድ ኢምንት ናቸው፤ በሰማይ መላእክትም ሆነ በምድር በሚኖሩ ሕዝቦች ላይ የፈቀደውን ያደርጋል፤ ፈቃዱን እንዳያደርግ ሊከለክለው የሚችል ወይም ‘ምን እያደረግህ ነው’ የሚለው ማንም የለም።


‘ይህን አድርግ’ ብሎ የሚያዘው፥ ወይም ‘ክፉ ሥራ ሠርተሃል’ ብሎ የሚወቅሰው ማነው?


ታዲያ፥ ‘እግዚአብሔር የሰውን አቤቱታ አይሰማም’ በማለት ለምን በእግዚአብሔር ላይ ታማርራለህ?


እግዚአብሔር በታላላቅ ሰዎች ላይ እንኳ ይፈርዳል፤ ታዲያ፥ ሰው ለእርሱ የፍርድን ዕውቀት ሊያስተምር ይችላልን?


ኢየሱስም እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና “ፈቅጃለሁ፤ ንጻ!” አለው። ለምጻሙም ወዲያውኑ ከለምጹ ነጻ።


በምኲራብ የነበሩትም ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቈጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios