ዘሌዋውያን 13:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ማንም ሰው የሥጋ ደዌ በሽታ ቢይዘው ወደ ካህኑ ያምጡት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ማንኛውም ሰው ተላላፊ የቈዳ በሽታ ከያዘው፣ ወደ ካህኑ ያምጡት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማናቸውም ሰው በለምጽ ደዌ ቢጠቃ እርሱን ወደ ካህኑ ያመጡታል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የለምጽ ደዌ በሰው ላይ ቢወጣ እርሱ ወደ ካህኑ ይሄዳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የለምጽ ደዌ በሰው ውስጥ ቢሆን እርሱን ወደ ካህኑ ያመጡለታል። |
“ማንም ሰው በሰውነቱ ላይ እባጭ ወይም ሽፍታ ወይም ቋቊቻ ቢታይና በገላው ላይ የሥጋ ደዌ ቢመስል፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ካህናት ከሆኑት ከልጆቹ ወደ አንዱ ያምጡት።