ዘሌዋውያን 13:49 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልኩም ወደ አረንጓዴነት ወይም ወደ ቀይነት ቢያደላ፥ የሚተላለፍ ሻጋታ ስለ ሆነ ለካህኑ ይታይ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በልብስ ወይም በዐጐዛ፣ በሸማኔ ዕቃ በተሠራ ወይም በእጅ በተጠለፈ ወይም ከቈዳ በተሠራ ዕቃ ላይ አረንጓዴ ወይም ቀይ መሳይ ደዌ ቢከሠት፣ እየሰፋ የሚሄድ ተላላፊ በሽታ ስለ ሆነ ካህኑ ይየው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደዌው በልብሱ ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም በተለፋው ቆዳ ወይም ከተለፋው ቆዳ በተሠራ በማናቸውም ነገር ላይ አረንጓዴ ወይም ቀይ ሆኖ ቢይታ፥ የለምጽ ደዌ ነው፤ ለካህኑ እዲያየው ይደረጋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደዌው በልብሱ ወይም በቆዳው ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከቆዳ በሚደረገው ነገር አረንጓዴ ወይም ቀይ ቢሆን፥ የለምጽ ደዌ ነው፤ ለካህኑ ያሳያል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደዌው በልብሱ ወይም በአጐዛው ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከአጐዛው በሚደረገው ነገር አረንጓዴ ወይም ቀይ ቢሆን፥ የለምጽ ደዌ ነው፤ ለካህኑ ይታያል። |
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ፥ ከለምጹ የዳነውን ሰው እንዲህ አለው፤ “ይህን ነገር ለማንም አትናገር፤ ነገር ግን ሄደህ መዳንህን ለካህን አሳይ፤ ምስክር ይሆንባቸው ዘንድ፥ ስለ መዳንህ ሙሴ ያዘዘውን መባ ለእግዚአብሔር አቅርብ” አለው።
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ ሲል አዘዘው፤ “ይህን ነገር ለማንም አትናገር፤ ነገር ግን በቀጥታ ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለሕዝብ ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ ያዘዘውን መሥዋዕት አቅርብ።”