ካህኑ ቊስሉን ይመርምር፤ በዙሪያው ካለው የሰውነት ቆዳ ይልቅ ወደ ውስጥ ጐድጒዶ በእርሱ ላይ የበቀለውም ጠጒር ወደ ቢጫነት በመለወጥ ስስ ሆኖ ከተገኘ የራስ ወይም የአገጭ ቈረቈር ወይም የሥጋ ደዌ ስለ ሆነ ያ ሰው ርኩስ መሆኑን ካህኑ ያስታውቅ።
ዘሌዋውያን 13:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑ እንደገና ይመርምረው፤ ቊስሉ በእርግጥ ተስፋፍቶ ከሆነ ሰውየው የረከሰ በመሆኑ ወደ ቢጫነት የተለወጠ ጠጒር መኖርና አለመኖሩ አስፈላጊ አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑ ይመርምረው፤ ቍስሉ በቈዳው ላይ ከሰፋ፣ ካህኑ የጠጕሩን ቢጫ መሆን አለመሆን ማየት አያሻውም፤ ሰውየው ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑ ያየዋል፤እነሆም፥ ቈረቈሩ በቆዳው ላይ ቢሰፋ ካህኑ ብጫውን ጠጉር አይፈልግም፤ እርሱ ርኩስ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆም፥ ቈረቈሩ በቆዳው ላይ ቢሰፋ ካህኑ ብጫውን ጠጕር አይፈልግም፤ ርኩስ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፥ ቈረቈሩ በቁርበቱ ላይ ቢሰፋ ካህኑ ብጫውን ጠጕር አይፈልግም፤ ርኩስ ነው። |
ካህኑ ቊስሉን ይመርምር፤ በዙሪያው ካለው የሰውነት ቆዳ ይልቅ ወደ ውስጥ ጐድጒዶ በእርሱ ላይ የበቀለውም ጠጒር ወደ ቢጫነት በመለወጥ ስስ ሆኖ ከተገኘ የራስ ወይም የአገጭ ቈረቈር ወይም የሥጋ ደዌ ስለ ሆነ ያ ሰው ርኩስ መሆኑን ካህኑ ያስታውቅ።
ነገር ግን በካህኑ አመለካከት ቊስሉ ካልተስፋፋና ጤናማ ጠጒርም በቅሎበት ከተገኘ፥ ቊስሉ የተፈወሰ ስለ ሆነ፥ ንጹሕ መሆኑን ካህኑ ያስታውቅለት።