እኔም እንዲህ ስል መለስኩ፦ “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ይህስ ከቶ አይሁን! እኔ ከቶ ረክሼ አላውቅም፤ ከሕፃንነቴ ጀምሮ የበከተ ወይም አውሬ የገደለው ከብትን ሥጋ የበላሁበት ጊዜ የለም፤ ጸያፍ ምግብም አልበላሁም።”
ዘሌዋውያን 11:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ይህን ለእስራኤል ሕዝብ ንገሩ፤ በምድሪቱ ከሚገኙት እንስሶች መብላት የምትችሉት እነዚህን ነው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እስራኤላውያንን እንዲህ በሏቸው፤ ‘በየብስ ከሚኖሩ እንስሳት ሁሉ የምትበሏቸው እነዚህ ናቸው፦ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብላችሁ ተናገሩ፦ በሕይወት ከሚኖሩ ከምድር እንስሶች ሁሉ የምትበሉአቸው እነዚህ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብላችሁ ንገሩአቸው፦ በምድር ካሉት እንስሳት ሁሉ የምትበሉአቸው እንስሳት እነዚህ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በሉአቸው፦ ከምድር እንስሶች ሁሉ የምትበሉአቸው እነዚህ ናቸው። |
እኔም እንዲህ ስል መለስኩ፦ “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ይህስ ከቶ አይሁን! እኔ ከቶ ረክሼ አላውቅም፤ ከሕፃንነቴ ጀምሮ የበከተ ወይም አውሬ የገደለው ከብትን ሥጋ የበላሁበት ጊዜ የለም፤ ጸያፍ ምግብም አልበላሁም።”
የሚበላ ምግብ ሁሉ ከሸክላው ዕቃ የውሃ ነጠብጣብ ቢያርፍበት፥ ርኩስ ይሆናል፤ የሚጠጣም ነገር ቢሆን በዚያ ሸክላ ዕቃ ውስጥ ካለ ርኩስ ነው።
ነገር ግን ከሚያመሰኩት ወይም ሰኮናቸው ስንጥቅ ከሆነው የሚከተሉትን አትበሉም፤ ግመል ያመሰኳል፤ ነገር ግን ሰኰናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ይሁን።
ባልተለመደ በልዩ ልዩ ዐይነት ትምህርት አትማረኩ፤ ልባችን የመብል ሥነ ሥርዓቶችን በመጠበቅ ሳይሆን በጸጋ ቢጸና መልካም ነው፤ ይህን የምግብ ሥነ ሥርዓት የተከተሉ ሰዎች ምንም አልተጠቀሙም።
እነዚህ ነገሮች የመታደስ ጊዜ እስኪመጣ ድረስ በሥራ ላይ የዋሉ አፍአዊ ሥርዓቶች ናቸው፤ እነርሱ ስለ መብልና ስለ መጠጥ፥ ስለ ልዩ ልዩ የመንጻት ሥርዓቶችም ብቻ የተደረጉ ናቸው።