ይሁዳ 1:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ሁሉ አስቀድማችሁ አንድ ጊዜ የምታውቁት ቢሆንም እንኳ ጌታ ሕዝቡን ከግብጽ አገር አውጥቶ እንዳዳነና ያላመኑትንም በኋላ እንዳጠፋቸው ላስታውሳችሁ እወዳለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምንም እንኳ አስቀድማችሁ ይህን ሁሉ የምታውቁ ቢሆንም፣ ጌታ ሕዝቡን ከግብጽ ምድር እንዴት እንዳወጣ፣ በኋላ ግን ያላመኑትን እንዳጠፋ ላስታውሳችሁ እወድዳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ሁሉን ነገር አንድ ጊዜ ያወቃችሁትን እናንተን፥ ጌታ ከግብጽ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ ጌታ ከግብጽ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ ጌታ ከግብፅ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ። |
ይህም ሆኖ የምትሰፍሩበትን ቦታ ለመፈለግና የምትሄዱበትን መንገድ ለማሳየት ቀን በደመና ሌሊት በእሳት፥ በፊታችሁ በሚሄደው በአምላካችሁ በእግዚአብሔር አልተማመናችሁም።
ወዳጆች ሆይ! ይህ የምጽፍላችሁ ሁለተኛው መልእክት ነው፤ ሁለቱንም መልእክቶች የጻፍኩላችሁ እነዚህን ነገሮች በማስታወስ ቅን አስተሳሰብ እንዲኖራችሁ ላነቃቃችሁ ብዬ ነው።